1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች እና የአዉሮጳ ስጋት

ዓርብ፣ መጋቢት 30 2008

የምሥራቅ አዉሮጳ ሃገራት ለስደተኞችን ድንበሮቻቸዉን ከዘጉ እና ጥብቅ ጥበቃ ማድረግ ከጀመሩ ወዲህ ከአፍሪቃም ሆነ ከመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚሰደዱት ወገኖች ዳግም ፊታቸዉን ወደ ደቡብ ኢጣሊያ ማድረጋቸዉ እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1ISB8
Italien Flüchtlinge Rettung Mittelmeer
ምስል picture alliance/dpa/ Italian Navy Press Office

[No title]

የጣሊያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ትናንት ከ300 የሚበልጡትን ባህር ዉስጥ ከመስጠም አድነዋል። ሌሎች ከ250 ሺህ እስከ 300 ሺህ የሚገመቱት ደግሞ አሁንም ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ሊቢያ ዉስጥ እንደተሰበሰቡ ይነገራል። የተሰዳጆቹ የጉዞ አቅጣጫ መለወጥ የአዉሮጳ ሃገራትን ስጋት ዉስጥ ከቷል። ጣሊያን የባህር ጠረፍ ግዛቶቿ የአዉሮጳም ጭምር መሆናቸዉን በማመልከት ትብብር እየጠየቀች ነዉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የሮም ዘጋቢያችን ተክለ እግዚእ ገብረ ኢየሱስን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አነጋግሬዋለሁ።

ተክለ እግዚእ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ