ስደተኞችን በመግደል የተጠረጠሩ መያዛቸዉ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 17 2006ማስታወቂያ
በጩቤ ተወግተዉና ተደብድበዉ ወደባህር የተወረወሩት ቁጥር ወደስልድሳ እንደሚጠጋ ጀልባዉ ዉስጥ የነበሩ የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ የገለፀዉ የካታኒያ ፖሊስ በደቡባዊ ላምፔዱዛ ከጀልባዉ ሞተር ከሚወጣዉ መርዛማ ጭስ የተነሳ መተንፈስ ሳይችሉ ቀርተዉ በመታፈን 29ሰዎችም መሞታቸዉንም አመልክቷል። ከስደተኞቹ የአንዱ ሕይወትም በካርቦን ሞኖክሳይድ ታፍኖ ወደሃኪም ቤት ሲወሰድ ማለፉም ተገልጿል።
ተኽለእዝጊ ገ/ኢየሱስ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ