1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኝነት በስደተኛዉ ብዕር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 15 2006

«ሁሌም ሰባት ቀን ሰርቼ ሶስት ቀን እረፍት፤ ሰባት ቀን ሰርቼ አራት ቀን ረፍት ቋሚ ፕላን ባለበት የኤርፖርት ስራዬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት እገባና ስድስት ሰዓት ሰርቼ ማታ ዘጠኝ ሰዓት እወጣለሁ፤ ማታ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ እጀምርና፤ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል የሚያልቅ የሁለት ሰዓት ሥራ እገባና እንደጨረስኩ፤

https://p.dw.com/p/1CygL
Symbolbild schreiben Konferenz Stift Hand
ምስል Fotolia/ThorstenSchmitt


ወደ ቤቴ የምትወስድኝን ከለሌቱ ስድስት ሰዓት ከሩብ ላይ ያለችዉን የመጨረሻዋን ባቡር እይዛለሁ። የምኖርበት ቦታ ሩቅ ስለነበር ወደ ቤቴ በምሄድበት ሰዓት አዉቶቡስ አይኖርም። በመሆኑም ሌሊት ሰባት ሰዓት ላይ ከባቡር ወርጄ ከሃያ ደቂቃ በላይ የእግር መንገድ ይጠብቀኛል። በተለይ ክረምት ሲሆን ከቅዝቃዜዉ ጋር ዝናብ ወይም በረዶ እየደበደበኝ እቤቴ ስገባ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ይሆናል።»
ሲሉ የግል የስደት ተሞክሮአቸዉን 174 ገጽ ባለቻት አነስተኛ መፅሐፍ አቅርበዋል። በጀርመን የስደቱ ዓለምን ከተቀላቀሉ 12 ዓመታትን አስቆጥረዋል። አቶ አስፋዉ በመጽሐፋቸዉ፤ በጀርመን በቆዩበት ዓመታት በማህበረሰቡ ያጋጣማቸዉን የተለያዩ ገንቢ ጉዳዮች እና ባህል ለአንባብያን ለማቅረብ፤ በተለይ ሥለ ጀርመናዉያን ያወቁትን ለማሳወቅ እንደሞከሩ ይናገራሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን ፀሀፊ አስፋዉ ከበደን እና ሌላ በጀርመን በስደት ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊን የግል አስተያየታቸዉን አንዲያካፍሉን ጋብዘናል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ