ስዊድንና የስደተኞች ኮታ በአዉሮጳ22 ሚያዝያ 2006ረቡዕ፣ ሚያዝያ 22 2006የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ምህፃሩ «ዩኤንኤችሲአር» ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ ከአዉሮጳ ሃገራት ስዊድን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ስደተኞችን መቀበሏን አመለከተ። እንደድርጅቱ ስዊድን በኮታ 1,900 ስደተኞችን ተቀብላለች።https://p.dw.com/p/1Brfjምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ በዚህም ከሌሎች መሰል የአዉሮጳ ሃገራት በዚህ ረገድ ግንባር ቀደም ሆናለች። ከተቀበለቻቸዉ ስደተኞች መካከልም ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያንም ይገኛሉ። የስዊድን የስደተኞች ኮታ ከሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት እንዴት ከፍ ሊል ቻለ? የስቶክሆልም ዘጋቢያችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ የሚመለከታቸዉን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል፤ ቴዎድሮስ ምሕረቱ ሸዋዬ ለገሠ ተክሌ የኋላ