ስዊስ ህዝቧና ኢትዮጵያዊዉ አቶ ምስጢረ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 23 2005ማስታወቂያ
አቶ ምስጢረ ኃይለ ሥላሴ ከዛሬ 35 ዓመት አንስቶ ስዊትዘርላንድ ነው የሚኖሩት ።
አቶ ምስጢረ ስዊዘርላንድ ከመሄዳቸው በፊት እስራኤል አሜሪካንም ነበሩ ። ከእነዚህ ሃገሮች ግን በሰላማዊነቷ በመረጋጋቷ ስዊዘርላንድን መርጠዋታል ።
ስዊዘርላንድ አቶ ምስጢረ ጋዜጠኝነት አጥንተዋል በንግድ አስተዳደርም የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው ። አሁን በሂሳብ አያያዝ ሥራ ላይ ነው የተሰማሩት ። በትርፍ ጊዜያቸውም በጋዜጠኝነቱ ሞያ ይሰራሉ ። መፅሄት ያዘጋጁ ነበር ለመጽሄቶችና ለአንዳንድ ድረ ገፆችም ፅሁፎችን ይልካሉ ። «አድማስ» ህትመቱ ከተቋረጠ ብዙ አመታት ያስቆጠረ የአቶ ሚስጥረ መፅሄት ነው።
አድማስ መታተሙ ቢቆምም አቶ ምስጢረ መፃፍ አላቋረጡም ። እንደ በፊቱም ባይሆን Ethiosport.com ለተባለ ድረ ገፅ ፅሁፎቻቸውን ያበረክታሉ ።
በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ