ስለዝግመታዊ ለውጥ፣ ሳይንሳዊና ሃይማኖታዊ አመለካከት፣
ረቡዕ፣ የካቲት 4 2001ማስታወቂያ
ሰው፣ የመፍጠር ክህሎት ባለው ብቸኛ ኀይል፣ (እግዚአብሔር) የተገኘ፣ ወይስ በዝግመታዊ ለውጥ አሁን ከሚገኝበት የማስተዋል ደረጃ ላይ የደረሰ ፍጡር ነው? ሥነ-ፍጥረትና ሃይማኖት በምን ይስማማሉ? በምንስ ይለያያሉ?ፍጡራን፣ በዝግመታዊ ለውጥ የተገኙ መሆናቸውን በምርምር ተመረኩዞ ማብራሪያ ያቀረበው የመጀመሪያው ዕውቅ ተመራማሪ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ነገ፣ የካቲት 5 ቀን 2001 ዓ ም፣ ልክ፣ 200ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ይታሰባል። ይህን መንስዔ በማድረግ በዓለም ዙሪያ የዝካሬ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ሲሆን እኛም ለዛሬ ስለታዋቂው እንግሊዛዊው የዝግመታዊ ለውጥ ነባቤ-ቃል ቀማሪ፣ ዳግመኛ የምንለው ይኖረናል።
T Y/SL
►◄