ስለአመጋገብዎ ምን ያህል ይጠነቀቃሉ?
ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2007ማስታወቂያ
እርስዎስ ስለሚመገቡት የምግብ ዓይነት አስበዉ ያዉቃሉ? ወይስ ቤት ያፈራዉ የተገኘዉ አቅም የፈቀደዉ በሚለዉ አባባል ብቻ? ዶቼ ቬለ በጤናና አካባቢ ሳምንታዊ ዝግጅቱ የስነምግብ ባለሙያ በመጋበዝ አመጋገብን በሚመለከት ጥያቄ እንድታቀርቡ አድማጮቹን በፉስ ቡክ ገጻችን አማካኝነት ጋብዟል። በርካቶች ስልክ ቁጥሮቻችሁን ብትጽፉልንም የብዙዎቻችሁ ስልኮች አይሰሩም፤ ወይም ሲጠራ አልተነሱም። በአጋጣሚዉ በተዉልን የስልክ መስመር ያገኘናቸዉን አድማጮች በዝግጅታችን እንዲሳተፉ እድል ሰጥተናል። የስነምግብ ባለሙያ እና የኢትዮጵያ የምግብና ስነምግብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪም ለጥያቄዎቻቸዉ ማብራሪያ ሰጥተዉልናል። የድምጽ ዘገባዉ ያድምጡት፤
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ