1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ፣ ምክር ከታዋቂ መምህር፤

ረቡዕ፣ ጥር 9 2004

ትምህርት ፣ በተለይም ሥነ ፍጥረታዊ የሳይንስ ዘርፎች፣ ሂሳብና «ኢንጂኔሪንግ»ንም ጨምሮ ፣ ለኤኮኖሚም ሆነ አጠቃላይ ግንባታ መሠረቶች መሆናቸው እሙን ነው።

https://p.dw.com/p/13laK

የተለያዩ ማዕድናትና ጥሬ ሀብቶች ባሏቸው አገሮች ዕውቀት ሲስፋፋ ፤ ዕድገቱ እጅግ ሊፋጠን ይችላል። አንዳንድ አገሮች ደግሞ አሉ፣ ፤ እንደ ጃፓንና ጀርመን የመሳሰሉ። ትልቁ ሀብታቸው ፣ ትምህርት ፣ ምርምር ፣ በተለይም ከፍተኛ የሳይንስ ምርምር ነው። የኢንዱስትሪ ምርቶቻቸው የዓለምን ገበያ፣ የሚያጥለቀልቀውም ፣ ኩባንያዎቻቸውና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ፤ ለአዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች የሚፈለጉ ወጣቶችን በማስተማር ጠንካራ ድጋፍ ስለሚሰጡ ነው። ይህን ከሞላ -ጎደል ኀያላኑ መንግሥታት ሁሉ ይፈጽሙታል። አንድ ጥሩ ምሳሌ፤ ባለፈው ኅዳር ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ በሳይንስ ፣ ሂሳብና ኢንጂኔሪንግ በማስተማር ለታወቁ ለ 9 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰሮችና ሌሎችም ባለሙያዎች ሽልማት መስጠታቸው ነው። ሽልማቱን ከተቀበሉት መካከል፤ሳይንስ በተለይም ፊዚክስ ኢትዮጵያን ለመሰለ አዳጊ ሀገር ሊሰጥ ስለሚችለው ጠቀሜታ ያነጋገርናቸው የዛሬው የሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅት እንግዳችን ፣ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ፣ በሰሜን ካሮላይና ፌደራል ክፍለ ሀገር የግብርናና ቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ሰሎሞን ቢልልኝ ናቸው።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ