1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሴቶች በስን-ጹሁፍ ተሳትፎ

ረቡዕ፣ መስከረም 15 2000

በአገራችን ሴት ፀሃፍት ወደ ስነ-ጹሁፉ አለም ብቅ ማለት ከጀመሩ ጥቂት አመታትን አስቆጠሩ። እንደ መረጃም አንድ ሁለት ፀሃፍት በስነ-ግጥም ዙርያ ዝናን ያተረፉ የተዋጣለት ስራቸዉን ያበረከቱ እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል

https://p.dw.com/p/E0m8
በእንግልት ላይ ላሉ እህቶች
በእንግልት ላይ ላሉ እህቶች

ከአገር እርቀዉ የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን ወደ አገራቸዉ መልክዐ- ምድር እና ታሪክ መለስ በማለት ትዝታቸዉን ከሚኖሩባቸዉ አገራት ባህልና ገጠመኝ ጋር እያዛመዱ ቅሪታቸዉን ስሜታቸዉን የታዘቡትን ይገልጻሉ የ 56 አመትዋ ወ/ሮ ለምለም ጸጋዉ ኑሮዋቸዉን በአሜሪካን ምድር ካደረጉ ሶስት አስርተ አመታትን አስቆጥረዋል። መተዳደርያቸዉን በህክምናዉ ሞያ አስተዳደር ዘርፍ ቢያደርጉም ለስነ-ግጥም ልዩ ፍቅር እንዳላቸዉ ይገልጻሉ። በትርፍ ግዜአቸዉ ስነ-ግጥምን እንደ ተወዳጅ ስራ በማድረግ ብዕርና ወረቀታቸዉን በማገናኘት በአሜሪካን በተለይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በርካታ የስነ-ግጥም መጽሐፍት ለአንባብያን አቅርበዋል።

በቅርቡ በሣዑዲ አረብያ አንገቷ ተቀልቶ ህይወቷ እንድያልፍ የተደረገችዉ ምስኪን ኢትዮጽያዊት ጉዳይ ከሂሊናቸዉ ሊጠፋ አለመቻሉን ሲገልጹ እንባ ይተናነቃቸዋል። ይህች ሴት በህይወት ብትኖር ኖሮ ምን ትል ነበር በማለት በስነ-ግጥማቸዉ ችግሯን ስቃያዋን ለማሳየት ሞክረዋል። በአራገችን በአንዳንድ ቦታ የሚታየዉን የግዳጅ ጋብቻ፣ የሴቶች ጭቆና፣ እና እንግልት የኢትዮጽያ ህዝብ ድምጽ በሚል የስነ-ግጥም መድብላቸዉ አስቀምጠዉታል። የባህል መድረካችን ወ/ሮ ለምለም ጸጋዉን በመድረኩ ጋብዞ ነበር።