ሳዲቅ ካን የመጀመሪያው ሙስሊም የለንደን ከንቲባ
ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008ማስታወቂያ
ባለፈው ሀሙስ ለለንደን ከንቲባነት በተካሄደ ምርጫ ያሸነፉት የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባ ርሳቸውና ቤተሰባቸው ያገኙትን እድል ሁሉም የለንደን ነዋሪ እንዲያገኝ እንደሚሹ አስታወቁ ። ከፓኪስታን ስደተኛ ቤተሰብ ለንደን ተወልደው ያደጉት ሙስሊሙ የሌበር ፓርቲ አባል ሳዲቅ ን እንዳይመረጡ ከተቀናቃኞቻቸው በተለይም ከወግ አጥባቂ ፓርቲ አመራርና አባላት ዘንድ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድባቸው ቆይቷል። የለንደኑ ወኪላችን እንደዘገበው ይህ በዘርና በሃይማኖት ላይ ያተኮረው ዘመቻ ቅሬታን አስከትሏል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ