ሳውዲ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ሁኔታ
እሑድ፣ ሰኔ 25 2009ማስታወቂያ
በሳውዲ ዐረቢያ አሉ ከሚባሉት ከሁለት ሚልዮን የሚበልጡት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው መካከል፣ ብዙዎቹ ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሄዱ የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያውያኑ ቁጥር ከ400,000 በላይ መሆኑ ይገመታል። እስካሁን የተመለሱት ግን በቁጥር ሲታይ ንዑስ ነው። 42,000 ገደማ ብቻ ነው። ወደ ሀገር የመመለሱ ሂደት፣ እንዲሁም፣ አሁንም በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙት ለመመለስ ተዘጋጅተው በመጠባበቅ ላይ ያሉት እና ገና ውሳኔ ላይ ያልደረሱት ሕጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ወገኖች ሁሉ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፣ ከፍተኛ ችግርም አጋጥሟቸዋል። አሳሳቢው የእነዚህ ዜጎች ጉዳይ እና የወደፊቱ እጣቸው ምን ሊሆን ይችላል? ውይይት አካሂደንበትል።
አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ