1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳንዲ እና መዘዟ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2005

ሳንዲ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ማዕበል የቀላቀለበት ኃይለኛ አዉሎ ነፋስ በምሥራቃዊ ዩኤስ አሜሪካ ብርቱ ቀውስ አስከተለ። ኒው ጄርሲ ፌዴራዊ ግዛት ደቡባዊ አካባቢ ሲደርስ እስከ 130 ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት የነበረው አዉሎ ነፋስ ከፊል ኒው ዮርክን አጥለቅልቋል።

https://p.dw.com/p/16ZgP
ምስል Reuters

በዚሁ ጊዜ ቢያንስ አሥራ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ኮሬንቲ ተቋርጦባቸዋል። ይኸው በዩኤስ አሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ከባድ መሆኑ በተነገረለት ማዕበልና ብርቱ አዉሎ ነፋስ ሰበብ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በስምንት ፌዴራዊ ክፍላተ ሀገር የአስቸኳይ ጊዜ ሲያውጁ፡ ኒው ዮርክንና ኒው ጄርሲን ዓቢይ ጥፋት የታየባቸው ብለዋቸዋል። ይህም በተለይ የኒው ዮርክ ከተማ እና በኒው ጄርሲ የአትላንቲክ ከተማ ነዋሪዎች ከፌዴራዊው መንግሥት ርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ክፍት አድርጎዋል። በኒው ጄርሲ አንድ የአቶም ኃይል ማመንጫ ተቋም ለጥንቃቄ ሲባል ተዘግተዋል። በዋሽንግተን እና በኒው ዮርክ መሥሪያ ቤቶች፡ የዎል ስትሪት አክስየን ገበያ ጭምር፡ እንዲሁም፡ ድልድዮች ዛሬ ለሁለተኛ ቀን የተዘጉ ሲሆን፡ በሰሜን ምሥራቃዊ ዩኤስ አሜሪካ የሕዝብ ማመላለሻ መሥመሮች ስራቸውን አቁመዋል፤ ወደ 15.000 የሚጠጉ በረራዎችም ተሰርዘዋል። የብርቱው አውሎ ንፋስ ሴንዲ መዘዝ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ አጋማሽ እስከ ካናዳ ባለው አካባቢ ወደ ሀምሣ ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎችን አስግቶዋል። ፕሬዚደንት ኦባማ ሴንዲ በሰው ሕይወት ላይ ጥፋት እንዳያደርስ የመከላከያውን ስራ ለማስተባበር ሲሉ አንድ ሣምንት የቀረውን የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዘመቻ አቋርጠዋል።
« በወቅቱ ሳንዲ በምርጫው ላይ ሊያስከትለው የሚችል መዘዝ አላሳሰበኝም። ማዕበሉ በቤተሰቦቻችን እና በሕይወት አድን ቡድኖቻችን ላይ ሊያስከትለው የሚችለው መዘዝ ነው እኔን ያሳሰበኝ። » በካናዳም ቢሆን በአውሎ ነፋስ ምክንያት አንዲት ሴት ለሞት ተዳርገዋል።

አርያም ተክሌ

ገመቹ በቀለ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ