1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳንባ ነቀርሳ-የዓለም ስጋት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 16 2000
https://p.dw.com/p/E0mW
ሳሉ ያዳክማል......
ሳሉ ያዳክማል......ምስል AP
የዓለም የጤና ድርጅት የሳንባ ነቀርሳ በሽታን ለመቆጣጠር የሚደረገዉ ጥረት ያመጣዉ ዉጤት ካለፉት ዓመታት ይልቅ መቀነሱ ጠቆመ። ድርጅቱ እንደሚለዉ በዓለም ዙሪያ ከሚታየዉ የሳንባ ነቀርሳ ስርጭት 61በመቶዉ ብቻ ነዉ በአግባቡ የታወቀዉ። ቀሪዉ ምርመራ ባላደረጉና ህክምና በማይከታተሉ ሰዎች አማካኝነት ህብረተሰቡን እየጎዳ ነዉ።