ሲየራ ልዮን እና የጦር ወንጀለኞችዋ
ቅዳሜ፣ የካቲት 21 2001ማስታወቂያ
ፍርድ ቤቱ ሶስት የቀድሞ የሲየራ ልዮን የተባባረው ዓብዮታዊ ግንባር የተሰኘው ዓማጽያን ቡድን መሪዎች በሀገሪቱ የርስበርስ ጦርነት ጊዜ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂዎች መሆናቸውን አራጋግጦ በቅርቡ ተገቢውን የቅጣት ብይን እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መልካም መሆኑን ቢያመለክትም፡ ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ብዙ የጦር ወንጀል ተጠርጣሪዎች አሁንም በነጻ በመዘዋወር ላይ መሆናቸው እንዳሳሰበው ገልጾዋል።
AI/RTRE
AA/HM