1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን ለኤርትራ የኤሌትሪክ ኃይል ልትሸጥ ነዉ መባሉ

ሰኞ፣ ግንቦት 11 2006

ሱዳን የኤሌትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ለመግዛት ዝግጅት ላይ መሆንዋ ይታወቃል። ባለፈዉ ሰምን አንዳንድ የብዙሃን መገናኛ ድረ-ገፆች እንደዘገቡት ደግሞ፤ ሱዳን ለኤርትራ የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሸጥ በዝግጅት ላይ ናት።

https://p.dw.com/p/1C2a5
Symbolbild Stromausfall Steckdose Mehrfachstecker Strom
ምስል BilderBox

አዲስ አበባ የሚገኘዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገ/ እግዚአብሄር ያነጋገራቸዉ አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እንደገለፁት፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛዉን የኤሌትሪክ ኃይል ለኤርትራ ልትሸጥ ነዉ መባሉ የራሱ አሉታዊ እና አዎንታዊ ገፆች አሉት። በወሎ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ ዳግም ወልደማርያም ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት፤ የተባለዉ ነገር እዉነት ከሆነ አካባቢያዊ የፖለቲካ ትብብርን ያጠናክራል፤ በጠላትነት የመከበብ ስሜትንም ያርቃል። ዝርዝሩን ዩሃንስ ገብረግዚአብሄር ያሳማናል።

ዮሃንስ ገ/ እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ