ሰይፍ አል ኢስላም እና የሄጉ ፍርድ ቤት17 ጥቅምት 2004ዓርብ፣ ጥቅምት 17 2004ባለፈው ሳምንት የተገደሉት የቀድሞው የሊቢያ መሪ የሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍይ አልኢስላም ጋዳፊ ፣ ለሄጉ ዓለም ዓቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድቤት እጃቸውን ለመስጠት እንደሚፈልጉ አንድ የሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት ባለስልጣን አስታወቁ ።https://p.dw.com/p/RtmZሰይፍ አል ኢስላምምስል dapdማስታወቂያ ስማቸው ያልተጠቀሰው እኙሁ ባለስልጣን ሰይፍ አል ኢስላም ከተጠለሉበት በረሃ ወደ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚወስዳቸው አውሮፕላን እንዲዘጋጅላቸው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ። ፍርድቤቱ በበኩሉ ሳይፍ አል ኢስላም ያሉበትን ቦታና ሃሳባቸውን ለማወቅና ለማጣራት በሞመከር ላይ መሆኑን አስታውቋል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ