ሰብአዊ መብትና ያልተቋረጠው የብሔረሰቦች ስሞታ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 27 2006ማስታወቂያ
ተደጋጋሞ የተወሳውና በመወሳትም ላይ ያለው አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረ 22 ዓመት ከመንፈቅ ገደማ በሆነው የ ኢ ህ አ ዴ ግ ዘመነ- መንግሥት ነው። የብሔረሰቦችን መብት በተመለከተ ቃልና ተግባር እስከምን ድረስ ተጣጥመዋል?። መሠረታዊው ግለሰባዊም ሆነ ማሕበረሰባዊው የመብት ይዞታ እንዴት ነው? ከተለያዩ አካባቢዎች ወደዚህ ራዲዮ ጣቢያ የሚላኩ የ SMS ና የድምፅም መልእክቶች እንደሚጠቁሙት፣ የመብት ጥያቄ እንደቀጠለ ነው። ለምሳሌ ያህል የቁጫና የሸካ ብሔረሰቦች የሚያቀርቡትን ስሞታ መጥቀስ ይቻላል። መጥቀስ ብቻ ሳይሆን፣ ባለሙያዎች ይወያዩበት ዘንድ ለዛሬ የውይይት ርእሳችን አድርገነዋል።
ተክሌ የኋላ