1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰርግ በጀርመን እና በዮናይትድ ስቴትስ

ሐሙስ፣ ግንቦት 8 2005

በብዙ ሀገራት ሰርግ የአጭር ወይንም የአንድ ቀን ድግስ ብቻ አይደለም። ትንሽ ለየት የሚያደርገው የሰርግ ስነ ስርዓቱ እና ቅድመ ዝግጅቱ ነው።

https://p.dw.com/p/18XwK
Ein frisch getrautes Ehepaar wird mit Reis beworfen. #7243780 - wedding rice © Marco Scisetti - Fotolia.com
Symbolbild Hochzeit Heirat Eheምስል Fotolia/Marco Scisetti

በዚህ በጀርመን ሰርግን «ሆህሳይት» ይሉታል። «የድግስ ጊዜ»።

ሙሽሪት ለምን የሰርጓ ቀን እቅፍ አበባ ትይዛለች? በዮናይትድ እስቴትስ ለምን ለሙሽሪት የስጦታ ድግስ ወይንም« ዌዲንግ ሻወር»ይዘጋጃል? ስትሉ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ከሆነ ለዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ በዛሬው የባህል መድረክ ይዘናል።

ከ30 አመት በላይ በጀርመን ነዋሪ የሆኑት ኢንጂነር እሸቱ ወንድአፍራሽ « ምንም እንኳን በጀርመን ቋንቋው አንድ ቢሆንም የሰርግ ስነ ስርዓቱ ይለያያል ይላሉ። እሳቸው በሚኖሩበት በኖርድ ራይንቬስትፌሊያ ፌደራላዊ ክፍለ ሀገር ስላለው የሰርግ ስነ ስርዓት ገልፀውልናል። በተጨማሪም በዮናይትድ እስቴትስ ለሙሽሪት ስለሚዘጋጀው የስጦታ ድግስ ወይንም« ዌዲንግ ሻወር» አመጣጥ ፣ የሰርጉ ቀን ሙሽሮች ታዳሚዎቹን ለማስደምም ስለሚያደርጉት ውዝዋዜ ወይንም ዳንስ እና ከሰርግ ጋ ለተያያዙ ሌሎች ጥያቄዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ በዮናይትድ እስቴትስ ያደጉት አዳም ገብሩም ያሉን አለ። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ