1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላም ያልሰፈነባት ጊኒ ቢሳው

ሰኞ፣ ጥቅምት 12 2005

የታጠቀ የጦር ሀይል ቡድን ትናንት በጊኒ ቢሳው የቢሳላንሳ የአየር ጦር ሰፈርን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ሙከራው ሊከሽፍ ቢችልም፤ በድርጊቱ ሰባት ወታደሮች ተገድለዋል።

https://p.dw.com/p/16Ugq
Das Bild zeigt einen toten Soldaten, der bei einem Angriff am Sonntag Morgen (21.12.) getötet wurde, als eine aufständische Militäreinheit die Luftwaffenbasis von Bissalanca attackierte. Diese Attacke konnte zurückgeschlagen werden, wobei sieben Soldaten gestorben sind. Copyright: DW/Braima Darame 21.10.2012, Bissau, Guinea-Bissau
ምስል DW

የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ትናንት ማምሻውን እንዳስታወቀው ቡድኑ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርጓል። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ ጊኒ ቢሳው ውስጥ ያለመረጋጋት እና መፈንቅለ መንግስት ተካሂዷል።

ጊኒ ቢሳው ውስጥ ቢያንስ በየስድስት ወሩ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ይካሄዳል። ከ10 ወራት በፊት ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኋላ ባለፈው ሚያዚያ የተካሄደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ስኬታማ ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትር ካርሎስ ጎሜሽ ጁኔር አመራር ስር በዲሞክራሲያዊ ሂደት የተመረጠው መንግስት በመጀመሪያ በወታደራዊ ም/ቤት ኃላም በሽግግር መንግስቱ ተተክቷል። ትናንት ደግሞ እንዲሁ ሌላኛው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መሆኑ ነው።

Das Bild zeigt den Generalstabschef der Streitkräfte von Guinea-Bissau, General António Indjai (im blauen Gewand) in einer Gruppe von regimetreuen Soldaten. Das Foto ist nach der Attacke aufständischer Militärs auf die Luftwaffenbasis von Bissalanca entstanden. Copyright: DW/Braima Darame 21.10.2012, Bissau, Guinea-Bissau
ጠቅላይ የታማጆር መሪ አንቶኒኦ ኢንድጃይ እና የጊኒ ቢሳው የጦር ኃይልምስል DW

ባለፈዉ ዓመት ታህሳስ ወር መንግስትን በኃይል ርምጃ ለመገልበጥ ከተደረገው እንቅስቃሴ በኋላ የፓለቲካ ምሁር ፓውሎ ጎርጃዎ እንዲህ አሉ፤ « የጦር ሀይሉ አወቃቀር ለማሻሻል ዕርምጃ እስካልተወሰደ ድረስ ለጊኒ ቢሳው ዘላቂ መፍትሄ ይገኛል ብዬ አልገምትም። ጊኒ ቢሳው ዉስጥ ስልጣን በሲቪሉ አመራር ሳይሆን በጦር ኃይሉ እጅ ነዉ። ሀገርቷ ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀችበት ጊዜ አንስቶ ያለውም ይኸዉ ነው።»

ያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ካርሎስ ጎሜሽ ጁኔር የመጀመሪያውን ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሲያሸንፉ የ2ኛው ምርጫ አሸናፊም ይሆናሉ ተብሎ ነበር የተገመተው። ይሁንና እውቅና የተሰጣቸው እኚሁ የሀገር መሪ የጦር ኃይሉን መዋቅር ሊለውጡ እንደሚችሉ ለወታደራዊው ኃይል ግልፅ ነበር። ጎሜሽ የጊኒ ቢሳውን የጦር ኃይል እንዲያሰለጥን የአንጎላ ወታደሮችን ወደ አገራቸው ሲያመጡም ይህ የሀገሪቱን የጦር ኃይል አላስደሰተም። ያኔም ጎሜሽን በመቃወም የሁለተኛውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አጣጥለው ለጦር ኃይሉ ተስማሚ የሆነ የሽግግር መንግስትን መረጡ። ከፖርቹጋል አለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም IPRIS የፓለቲካ ምሁር ፓውሎ ጎርጃዎ- የጦር ሀይሉ መዋቅር ተቃውሞ ያስነሳበትን ምክንያት ሲያብራሩ።

Generalstabschef von Guinea-Bissau - António Indjai. Das Bild zeigt den Generalstabschef der Streitkräfte von Guinea-Bissau, General António Indjai. Er war einer der Hauptverantwortlichen für den Putsch vom April 2012, bei dem die Regierung unter Premierminister Carlos Gomes Junior abgesetzt wurde. Copyright: DW/Braima Darame 22.10.2012, Bissau, Guinea-Bissau
በሚያዝያ በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጠቅላይ የታማጆር መሪ አንቶኒኦ ኢንድጃይምስል DW

«በመጀመሪያ ነገር ለጦር ሀይሉ አወቃቀር የሚታገሉት አንጋፋዎቹ የጦር ኃይል አባላት ናቸዉ። ከነዚህ ወታደሮች ከፊሉ ከፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ለመላቀቅ የታገሉ ናቸው። ከነዚህ አብዛኞቹም ዛሬ የጦር ኃይሉ ቁልፍ ቦታዎችን ይዘዋል። ስለሆነም በነፃነት ትግሉ ዉጤት ከበሬታ ያገኙ ናቸው። የጦር ኃይሉ መዋቅር መሻሻል ካለበት ደግሞ ከጦር ኃይሉ መሰናበት ያለባቸው እነዚሁ ሰዎች ይሆናሉና » የሀገሪቱ የጦር ኃይል ዛሬም ጠንካራ ነው። ምንም እንኳን የጊኒ ቢሳው የጦር አይሮፕላኖች በስራ ላይ ከዋሉ አመታት ቢቆጠሩም በጥሩ ይዞታ ላይ ይገኛሉ።

በጊኒ ቢሳው ከመጨረሻው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ሁኔታዎች የተረጋጉ ቢመስሉም በሀገሪቱ ብዙ የአመፅ ርምጃዎች ተካሂደዋል። እኢአ 2009 የያኔው ፕሬዚዳንት ኒኖ ቪአራ እና የቀድሞው የጦር ኃይል ጠቅላይ የታማጆር መሪ -ታግሜ ና ዋዬ በተሰነዘረባቸዉ ጥቃት ነበር የተገደሉት። የሁለቱም የግድያ መንስኤ እስካሁን ድረስ ይፋ አልሆነም። እንደ ፈረንሳይ የዜና ወኪል አዣንስ ፕረስ ገለፃ ከሆነ የእሁዱ ጥቃት አስተባባሪ ፓንሳዎ ቻማ በፕሬዚዳንት ኒኖ ቪአራ ግድያ እጃቸዉ አለ። የሀገሪቱ ጊዜያዊ መንግስት በበኩሉ በጊኒቢሳዉ ላለዉ አለመረጋጋት ፖርቱጋልና የፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች ተጠያቂ አድርጓል። በጊኒ ቢሳው ያለው አለመረጋጋት የሚያመላክተው በፍጥነት በሀገሪቷ ሰላም እንደማይሰፍን ነው።

ዮሀንስ ቤክ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ