ሰላማዊ ሰልፍ በብራስልስ
ዓርብ፣ ግንቦት 26 2008ማስታወቂያ
ዛሬ ብራስልስ ቤልጅየም ከሚገኘዉ የኅብረቱ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ኢትዮጵያዉያን አሁንም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ግድያ፣ እሥራት፣ እና ማዋከብ ይፈጸማል ሲሉ ድርጊቱን አዉግዘዋል።
በሰልፉ ላይ ከቤልጅግ፤ ከጀርመን፤ ከፈረንሳይ፤ ከሆላንድ፤ ከጣሊያን፣ ከስዊድንና ከሌሎችም የአዉሮጳ ሃገራት የመጡ ወገኖች መገኘታቸዉን ተገልጿል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በተወካዮቻቸዉ አማካኝነት አቤቱታቸዉን በደብዳቤ አስፍረዉ ለአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ማቅረባቸዉን ሰልፉን ተገኝቶ የተመለከተዉ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን ገልጾልናል።
ሸዋዬ ለገሠ/ገበያዉ ንጉሤ
አርያም ተክሌ