ሰለ ታሰሩት ጋዜጠኞች የስዊድን መንግሥት ምላሽ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ ሽብርተኝነትን በመደገፍና ድንበር ዘልቆ ያለህጋዊ ፈቃድ በመግባት ጥፋተኛ ናቸዉ የተባሉትን ሁለት ስዊድናዉያን ጋዜጠኞች ጉዳይ በሚመለከት የስዊድን መንግስት የሚጠበቅበትን ያህል ጥረት አላደረገም የሚል ትችት እየተሰነዘረበት ነዉ።ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየ እና ፎቶ ጋዜጠኛ ዮሃን ፐርሰን ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የፊታችን ማክሰኞ ብይን እንደሚሰጥ ይጠበቃል። የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን መንግስታቸዉ በተለይም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጠኞቹን ለመከላከል ተገቢዉን ጫና አላደረገም በሚል ቅሬታቸዉን እያሰሙ ነዉ። የዶቼ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ይህን አስመልክቶ የስዊድን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን አነጋግሯቸዋል ።
ማንተፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ