ሮቤል ተመስገን
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2004ማስታወቂያ
በሳምንቱ መጀመሪያ የዓለምእጅግ የተከበሩ ሎሬትሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። «የዓለምእጅግ የተከበረ ሎሬት» የሚል ማዕረግ የተሰጣቸዉን አፈወርቅ ተክሌ በስዕል ጥበብ እዉቀተቻዉና በምርጥ ስዕሎቻቸዉ ከኢትዮጵያ አልፈዉ በዓለም የሥነ-ጥበብ መድረክ የመጨረሻ ጫፍ የደረሱ ክቡር የጥበብ ሰዉ ነበሩ። ወጣት ሰዓሊያን ከሳቸው ምን መማር ችለዋል? አድናቂያቸው ወጣት ሰዓሊ ሮቤል ተመስገን አርዓያዬ ከሚላቸው ዝነኛ ሰዓሊ ስለተማረው እና ስለ ራሱ ስራዎች ያጫውተናል።
ሮቤል ወደ ጀርመን በርሊን ብቅ ብሎም በአንድ «ሰርቫይቭአርት» የስዕል አውደ ርዕይ ላይ ተካፍሏል። ከሌሎች ኢትዮጵያን ሰዓሊዎች ጋ ተወዳድሮ ወደ ጀርመን ከመጡት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሰዓሊያን አንዱ ነው። ያተኮረበትም ርዕስ «ሴት እና ወንድ» ይሰኛል። በቪዲዮ መልክ የቀረበ ስነ ጥበብ ነው። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ሮቤል ጋቢ ለብሶ የተነሳውን ፎቶ የተመለከትን አንጠፋም። ይህንንም ሆን ብዬ ነው ያደረኩት ይላል። ሚስጥሩን አካፍሎናል። ሁሉንም ከዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ