ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላለፉ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 16 2009ማስታወቂያ
የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓመታዊዉ እና ባህላዊዉ የገና ንግግራቸዉ በሶርያ እየተካሄደ ስላዉ አሰቃቂ የሰብዓዊ እልቂት ላይ ነበር ያተኮሩት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት በሶርያ የሲቪል ማኅበረሰቡ አስቸኳይ ርዳታ ይሻል፤ የርስ በርስ ጦርነት በተዘፈቀችዉ ሃገር በሶርያ የሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ እየተካሄድ ያለዉ የሰብዓዊ ጥሰቶች ይቁሙ ሲሉ በቫቲካን ቅዱስ ፔተር አደባባይ ላይ ለተሰበሰበዉ ወደ 40,000 የሚጠጉ ምዕምናን በታደሙበት ተናግረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በአዉሮጳ በተለያዩ ጊዜያቶች በተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች የተገደሉ ሰለቦችንም በፀሎታቸዉ አስበዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኡርቢ ኤታ ኦርቢ» «ለከተማዉና ለዓለም» የተሰኘዉን ዓመታዊ የገና መልእክት አስተላልፈዋል።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ