1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2008

የሮማ ካቶሊካዊት ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የኪዩባ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ፤ ወደ ዩኤስ አምርተዋል። በዩኤስ አሜሪካ በጉጉት እየተጠበቁ ነዉ። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸዉ ፕሬዝደንት ባራካ ኦባማን ጨምሮ ከተለያዩ የሐገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይነጋገራሉ።

https://p.dw.com/p/1GajX
Besuch von Papst Franziskus in Kuba und den USA
ምስል picture-alliance/dpa/C. Fusco

[No title]

የሮማ ካቶሊካዊት ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኩባዉያን ለ«አዲስ» ላሉት አብዮት እንዲነሱ ዛሬ መከሩ ። ፍራንሲስ የኩባ ኮሚኒስታዊ አብዮት መነሻ በሆነችዉ ሳንቲያጎ ደ ኩባ በመሩት የአደባባይ ፀሎት እንዳሉት ኩባዉያን አዲስ እና የመግባባት አብዮት ማድረግ አለባቸዉ። ኩባን ወደ ሐይማኖት የለሽ ኮሚንስታዊ ሥርዓት የቀየረዉ ሕዝባዊ አብዮት ለድል የበቃዉ እንደ ጎርጎሮያዉያኑ አቆጣጠር በ1959 ሳንቲያጎ ደ ኩባ በተደረገዉ ትግል ነበር።የሮማ ካቶሊካዉያኑ መንፈሳዊ መሪ በመሩት የአደባባይ ፀሎት ላይ የኩባዉ ፕሬዝደንት ራዑል ካስትሮ ተገኝተዉ ነበር።ርዕሠ ሊቃነ ፓጳጳሳት ፍራንሲስ በኩባ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቅቀዉ ማምሻቸዉን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተሻግረዋል።ፍራንሲስ በዩናይትድ ስቴትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያደርጉትን ጉብኝት፤ የፕሪስተን ዩኒቨርስቲ የሐማይማኖት ጉዳይ አጥኚ ሮበርት ጆርጅ እንደሚሉት፤ የአሜሪካ የካቶሊክ እምነት ተከታይ በጉጉት እየጠበቀዉ ነዉ።«የርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሱ ጉብኝት ከፍተኛ ጉጉት ነዉ የፈጠረዉ።እንዲያዉ ከንፋሱም ትረዳለሕ።የእሳቸዉን ቃላት ለመስማት ብዙዎች እየጠበቁ ነዉ።ለሰዉ ልጅ በሙሉ የተስፋና የፍቅር መልዕክት ይዘዉ እንደሚመጡ ይጠበቃል።»

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸዉ ፕሬዝደንት ባራካ ኦባማን ጨምሮ ከተለያዩ የሐገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይነጋገራሉ።ለዩናይትድ ስቴትስ ተጣማሪ ምክር ቤትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር ያደርጋሉም።

በዩኤስ አሜሪካ በጉጉት እየተጠበቁ ያሉት ርዕሠሊቃነጳጳሳትፍራንሲስን በተመለከተ የብዙኃን መገናዎች ምን እየዘገቡ ነዉ ሕዝቡስ ምን ይላል? የዋሽንግተኑን ወኪላችን ጠይቀነዉ ነበር።

መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ