1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሰየሙዋቸው ካርዲናሎች

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2007

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም ዙርያ ከሚገኙ ሃገራት የተዉጣጡ 20 ጳጳሳትን ፤ ካርዲናል ብለው ትናንት ሰይመዋል።

https://p.dw.com/p/1EFHc
Symbolbild Papst ernennt neue Kardinäle 4.1.2015
ምስል Andreas Solaro/AFP/Getty Images

ከ80 ዓመት እድሜ በታች ከሆኑት ተሰያሚ 20 ቄሶች መካከል 15ቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ፤ በሞት አልያም በተለያዩ ምክንያቶች ቦታቸዉን ቢለቁ ሊተኩዋቸዉ እንደሚችሉ ተዘግቧል። ጳጳሳቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከኢጣልያ፣ ከፈረንሳይ፣ ከፖርቹጋል፣ ከኒዉዚላንድ፣ ከቬትናም፣ ከሜክሲኮ፣ ከማይናመር፣ ከታይላንድ፣ ከኡራጉዋይ፣ ከስፔን፣ ከፓናማ፣ ከካፕቬርዴ እና ከቶንጋ የተዉጣጡ መሆናቸዉ ተመልክቶአል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ ጳጳስን ጨምሮ፤ ሶስት ጳጳሳትን ከአፍሪቃ ሰይመዋል። አዲስ የተሰየሙት ካርዲናሎች ሚና ምንድን ነው? ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተሰየሙትስ ጳጳስ ማን ናቸው፤ ሮም የሚገኘው ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግረንዋል

ተክለ እዝጊ ገብረየሱስ

ልደት አበበ