ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ አሸናፊዎች
ሐሙስ፣ መስከረም 12 2009ማስታወቂያ
ሽልማቱን የሚሰጠው እጎአ በ1980 ዓም የተቋቋመው የስዊድኑ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ለዚሁ አማራጭ ኖቤል ብሎ ለሚጠራው ሽልማት ዘንድሮ አራት አሸናፊዎችን መምረጡን ዛሬ በስቶክሆልም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። አሸናፊዎቹ ለደህንነታቸው ሳይሰጉ በሶርያ፣ ግብፅ፣ ሩስያ እና ቱርክ ለሰብዓዊ መብት እና ለፕሬስ ነፃነት ማስከበር ላደረጉት አስተዋፅዖ ለሽልማት መብቃታቸው በጋዜጣዊ መግለጫው ተነግሮዋል።
ቴድሮስ ምሕረቱ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ