ሩሲያ ጋዟን ዳግም ትለቃለች
ሰኞ፣ ጥር 11 2001ማስታወቂያ
ሩሲያ ቀደም ሲል በዋጋ አልፎም በጋዝ ስርቆት ስትከሳት በከረመችዉ ዑክሬን ላይ የጋዝ ፍሰቱን የሚቆጣጠር ታዛቢ አካል በመስመሮቹ አኳያ የማድረግ እቅድ የነበራት ቢሆንም ለጊዜዉ ግን ካለምንም ተቆጣጣሪ ቧንቧዉን ልትከፍት ትችላለች ነዉ የተባለዉ። በአንዳንድ የአዉሮጳ አገራት የተቋረጠዉ ጋዝ ፍሰት ባስቸኳይ እንዲቀጥል አበክሮ ያሳሰበዉ የአዉሮጳ ኅብረት የሩሲያና የዑክሬን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከተፈለገዉ ስምምነት የሚያደርሳቸዉን ዉይይት ማካሄዳቸዉን ደግፏል። ለጋዙ መቋረጥ የቀረበዉ ሳቢያና የተከተለዉ ዉጤት ግን እንዳሳሰበዉ አልሸሸገም።