1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሩር-የ2010 የአዉሮጻ የባህል ማዕከል

እሑድ፣ መጋቢት 12 2002

የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም እዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት የሚገኘዉ የሩር አካባቢ በመባል የሚታወቀዉ ሰፋ ያለ ክልል የአዉሮጻ የባህል ማዕከል በመሆን ተመርጦአል።

https://p.dw.com/p/MYYk
ምስል dpa

አካባቢዉ በሚገኘዉ የሩር ወንዝን ስያሜ ይዞ ያለዉ አካባቢ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን በጀርመን ዉስጥ ካሉ አካባቢዎች ሁሉ በርካታ ህዝብን አቅፎ በመያዙ ከአገሪቱ አንደኛ፣ በመሆን ከአዉሮጻ አገሮች ደግሞ ከፈረንሳይ እና ከእንግሊዝ ቀጥሎ የሩር አካባቢ በሶስተኝነት ይታወቃል። የሩር አካባቢ በርካታ ኢንዱስትሪን አቅፎ የያዘ በተለይም የብረት ማምረቻ እና የድንጋይ ከሰል መአድን የሚወጣበት አካባቢ በመሆኑ ነበር በርካታ ነዋሪዎች በአካባቢዉ የሰፈሩት። የከሰል ድንጋይ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ሲሄድ ይህ ሰፊ ግዛት ያቀፈዉ የኢንዱስትሪ ክልል እየተዘጋ አካባቢዉ ላይ ሰፍረዉ የሚገኙ ህዝቦች ስራ አጥ እየሆኑ፣ ገሚሱ አካባቢዉን እየለቀቀ ቆይቶአል። የአካባቢዉ ነዋሪዎች እና የአገሪቷ መንግስት ሁኔታዉን በማጤን ይህን ስራ የፈታ ፋብሪካ እና የኢንዱስትሪ ክልል የተለያዩ መስዕቦችን በማድረግ፣ እራሱን ፍብሪካዉን መማደስ ቦታዉን የመዝናኛ ታሪካዊ ሙዚየም አድርጎታል። ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ በዶቸ ቬለ ራድዮ የተለያዩ የቋንቋ ስርጭት ክፍል የሚገኙ የባህል መድረክ አዘጋጆች ቦታዉን ሲጎበኙ የአማራኛዉም ክፍል አንዱ ታዳሚ በመሆን ተገኝቶ በዛሪዉን እለት የባህል ጥንቅር በዚሁ ርእስ ዙርያ አድርጎታል መልካም ቆይታ።
ከዶቸ ቬለ ራድዮ ከተለያዩ ቋንቋ ክፍሎች የተዉጣጡ ሃያ ያህል የባህል መድረክ አዘጋጆች እና ሁለት የፎቶግራፍ ሰዎች በአንድ አነስ ባለ አዉቶቡስ ተጭነን የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም የባህል ማእዕከል ዋና ከተማ ወደ ተሰኘችዉ ወደ ኤሰን ከተማ ያመራነዉ። የራድዮ ጣብያችን ከሚገኝበት ከቦን ከተማ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ የዘንድሮዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት የባህል ማእከል ዋና ከተማ ኤሰን ከተማ ዳርቻ ላይ የሚገኘዉን እና መቶ ኤክታር ክልል ላይ የሚገኘዉን ቀደም ሲል በአለም ድንቅ እና ዉብ ይሰኝ የነበረዉ የድንጋይ ከሰል ማዉጫ ትልቅ ኢንዱስትሪ የዛሪዉን የኢንዱስትሪ ቤተ-መዘክር ነበር የጎበኘነዉ። መቶ ሄክ ታር መሪት ላይ የሚገኘዉ ይኸዉ የባህል ማዕከል ከተለያዩ አገራት የሚመጡ ቱሪስቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል። ሶስት ትዉልድን ያሳለፈዉ ይሕ ግዙፍ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ኢንዱስትሪ እንደ አዉሮጻዉያኑ 1847 አ.ም ተገንብቶ የመጀመርያዉን የድንጋይ ከሰል ማምረት የጀመረዉ። ጀርመናዉያን ጥቁሩ ወርቅ የሚል መጠርያ የሰጡት የድንጋይ ከሰል በአስራ ዘጠነኛዉ ክፍለ ዘመን የአገሪቷ የኢኮነሚ ዋልታ ሆኖ መቆየቱን የዘመኑ ትዉልድ እንዲያዉቀዉ ያለፉትንም አባቶች በምን ያህል ትልቅ ጉልበት እና ጥንካሪ አገራቸዉን እዚህ ማድረሳቸዉን ለማመስገን በአሁኑ ግዜ ቤተ መዘክር ሆኖ ለአለም አገራት ታሪኩን ያሳያል።
እንደ አዉሮጻዉያኑ ከ 2000አ,ም ጀምሮ የድንጋይ ከሰል በማምረቱ ሳይሆን በቤተ መዘክርነቱ በቱሪስቶች የሚጎበኘዉ ይህ እጅግ ግዙፍ የሆነዉ የባህል መድረክ፣ አካባቢዉ ጸድቶ የተለያዩ አረንጓዴ ተክሎች ተተክለዉ፣ ያ የነበረዉ ፋብሪካ ድንጋይ ከሰል ከአፈር እና ከአሸዋ መለያዉ የፋብሪካ ቁሳቁሱ ቆሞ እንዴት ይሰራ እንደነበር እንዴት ከመሪት ይወጣ እንደነበር፣ የአይን ምስክር የሆኑት መለዮአቸዉን አድርገዉ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ዉስጥ የሚደረገዉን ለየት ያለ ባርኔጣ አድርገዉ ሊያስጎበኙን ጀመሩ።
የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም የባህል ማእከል ተብሎ የተሰየመዉ የሩር አዉራጃ 53 ያህል መጠነኛ የሆኖ ከተሞችን አቅፎ 5.3ሚሊዮን ህዝብ እንደሚኖርበት ጥናቶች ይገልጻሉ። በዘንድሮዉ በዚህ በአዉሮጻ ማእከል ከአዉሮጻ እንዲሁም ከሌሎች አለማት የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ስራዎቻቸዉን ለአለም ህዝብ የሚያቀርቡበት የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ለያዝነዉ አመት መረሃ-ግብሮችን አዉጥቶአል። አፍሪቃዉያን ቻይናዉያን፣ ራሽያዉያን ታዋቂ ሰአሊዎች የኪነጥበብ ሰዎች ስራዎቻቸዉን የሚያሳዩበት መድረክ መግብያ ትኬት ተሸጦ አልቆአል።
በመቶ የሚቆጠሩ አመታቶች በድንጋይ ከሰል እንዱስትሪ ተዉጦ የነበረዉ ይህ ሰፊ አዉራጃ ከ170 የተለያዩ አገራት የመጡ የዉጭ አገር ዜጎች መኖርያም እንደሆነ ይነገራል። ቦታዉ በኢንዱስትሪ ዳብሮ የስራተኛ ጉልበት እጅግ እጥረት በነበረበት ወቅት ከቱርክ ከቻይና ከሰሜን አፍሪቃ አገራት ድንጋይ ከሰል ፋብሪካ ዉስጥ ተቀጥረዉ ለመስራት ወደ አገሪቷ ገብተዋል። በዚህም የሩር አካባቢ ከተለያዩ አለም አገራት የመጡ ህዝቦች ምንም እንኻ የጀርመንኛ ቋንቋ እጥረት ችግር ቢደርስባቸዉም ቦታዉን የአገሪቷ ዋንኛ የኢኮነሚ ምንጭ አድርገዉታል። በዚህም ይህ የድንጋይ ከሰል ተፈላጊነቱ ሲቀንስ እና በቦታዉ የቆሙት ግዙፍና መለስተኛ ፋብሪካዎች ሲዘጉ አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩ የገቢ ምንጫቸዉ ፋብሪካዉን አድርገዉ የነበሩ ህዝቦች ስራ አጥ እየሆኑ አልያም ወደ ሌላ አካባቢዎች ይፈልሱ ጀመር። የፋብሪካዎች መዘጋት በጀርመን ከፍተኛ ስራ አጥ ህዝቦች ቁጥር የሚኖሩበትም ቦታ አድርጎታል።
ዶርትሙንድ ኤሰን ዱሱርግ እና ቦሁም በሩር አዉራጃ የሚገኙ ዋና ዋናዎቹ ከተሞች በመሆን ይታወቃሉ። በዚህ በሩር ዙርያ ከ170 የተለያዩ የአለም አገራት የመጡ 562 ሺ ያህል የዉጭ አገር ዜጎች እንደሚኖሩ የዛሪ ሁለት አመት የተደረገዉ የመዘርዝር ጥናት ያሳያል። በአካባቢዉ 19 ያህል በጀርመን ታዋቂ ዩኝቨርስቲዎች የሚገኙበት፣ 1250 ቤተ-ክርስትያኖች እንዲሁም 180 ያህል መስጊዶች የታነጹበት በርካታ ህዝቦች በአንድ ተሰባብስበዉ የሚኖሩበት የጀርመን ክልል መሆኑ ተገልጾአል።

Deutsche Welle Pressereise RUHR.2010 mit Bernd Riegert
ምስል DW

የዶቸ-ቬለ የጎቭኝዎች ቡድን የአዉሮጻን የዘንድሮዉ የባህል ማእከል የስምንት ሰአታት እየተዘዋወረ ቢጎበኝም እሩቡን ያህል ቦታ ጠንቅቀን ለማየት ግዜዉ አላዳረሰንም። ቦታዉ እጅግ ሰፊ ነዉ የጥንቱ የማእድን ማዉጫ ጉድጓድ ገሚሱ የመዋኛ ስፍራ ሲሆን ሌላዉ የፊልም ማሳያ፣፡መድረክም ሆኖ ያገለጋል፣ በከፊል እንደዋሻ፣ አይነት ቅርጽ ኖሮት የማእድን አዉጭዎቹ ይለብሱት የነበረዉን መለዮ፣ ይጽፉት የነበረዉን ማስታወሻ ደብተር ይጠቀሙበት የነበረዉን የተለዩ ቁሳቁሾች በማስቀመጥ እና ልዮ በሆነ ቴክኖሎጂ በፈጠራቸዉ መብራት እና ኮንፒዉተሮች በማስደገፍ ልዮ ሙዚየም ሰርተዉበታል። የሚገርመዉ ይህ ለበርካታ አመታት ስራ ፈቶ የነበረ ኢንዱስትሪ በድጋሚ በርካታ የስራ ቦታን ፈጥሮ በሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች ሲተዳደሩበት ማየቱ ነዉ። በሌላ በኩል የከሰል እና የአቧራ ቦታ የነበረዉ ቦታ ጸድቶ እና አረንጓዴ ለብሶ ማራኪም ሆንዋል። ሶስት ትዉልድን ያገለገለዉ ኢንዱስትሪም ሳይፈርስ ታድሶ የታሪክ ማህደር ሆኖ በመቆም ትዉልድን እያመሰገነ ለአዲሱ ትዉልድ ታሪክን እየመሰከረ እንደገና በአዲስ ሃሳብ እና የስራ ቦታ የገንዘብ ገቢን በማስገኘት የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ ባህላቸዉን የሚያስተዋዉቁበት ሰፊ ማዕከል ሆኖ መገንባቱ እዉነትም ጀርመናዉያን አዲስ ሃሳብ አፍላቂዎች እና ትጉዎች ያሰኛቸዋል።

Flash-Galerie Polen im Ruhrgebiet
ምስል DW

አዜብ ታደሰ