ረሐብ በኢትዮጵያ ምክንያቱና መፍትሔዉ ክፍል II
ሐሙስ፣ ነሐሴ 22 2000ማስታወቂያ
ግማሽ ሚሊዮን ያክል ኢትዮጵያዊ መግደሉ ከሚገመተዉ ከ1977ቱ ረሐብ የተረፈዉ ፣-አሕያ መጣች ተጭና ምስር፣ እናትዬዋ ሞታለች ከሥር፣ ልጁ ይጠባል የረጋ ደም ሥር እያለ፣ ረሐብ ሥለገደላት ብጤዉ፣ መኖር-መዳኑ ስለማይታወቀዉ የረሐብተኛ ሞት ረሐብተኛ ልጅ አረዳ።የሰባ-ሰባቱ ሕፃን ሰማንያ ሰባት ለመራብ መድረስ አለመድረሱ እንደማይታወቅ ሁሉ የሰባ-ሰባቱ አርጂ በ1966ቱ ረሐብ ከሰባ-ሰባቱ ሕፃን መለየት-አለመለየቱም አይታወቅም።አንድ ነገር ግን ይታወቃል።ኢትዮጵያ የተራበ ዜጋዋ ቀድሞት ሥለተራበ ታላቁ፣ ረሐብ ሥለገደለዉ አቻዉ፣ ረሐብ ሥለሚጠብቀዉ ታናሹ እንደተናገረባት ስልሳ-ሰባ ዘመን እንደቆጠረችአለች።ዘንድሮም -አስር ሚሊዮን ረሐብተኛ ይቆጠርባታል።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ዘመን-ረሐብተኛዉን እየቆጠርን ስለማይልቀዉ ታሪክ ሳምንት የጀመርነዉን ዛሬ እንጨርሰዉ።