ሦስቱ የአዉሮጳ መሪዎች ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008ማስታወቂያ
ትናንት በኢጣልያዋ የቬንቶቴን ደሴት ተሰበሰቡት የሦስቱ ሃገራት መሪዎች በአዉሮጳ ስላለዉ የስደተኞች ቀዉስና፤ በፈረንሳይና ጀርመን ከደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ ስላለዉ የድኅነት ጉዳይ ላይ መነጋገራቸዉ ተዘግቦአል። በኤኮኖሚ ጉዳይ ላይም ያተኮረዉ የሦስትዮሹ ስብሰባ በተለይ በከፍተኛ ብድር ዉስጥ የተዘፈቀችዉ ኢጣልያ፤ ከባንክ በተገናኘ ጉዳይ ላይ ላላ ያለ ሁኔታ እንዲገጥማት ከኅብረቱ ይበልጥ ድጋፍ እንድታገኝ ጥረት እንደምታደርግ ተገልጾአል። በጣልያን ሮም የሚገኘዉ ወኪላችን ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር ዘገባ ልኮልናል።
ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ