1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሥራአጥ ፈላስያንና የአውሮፓ ሕብረት ፍ/ቤት

ረቡዕ፣ ኅዳር 3 2007

የአውሮፓ ፍርድ ቤት ትናንት ሉክስምቡርግ ላይ ባስቻለው ችሎት የጀርመን መንግሥት ፣ ኤልሳቤት ዳኖቭ ለምትባለው ሩሜኔያዊት የስራ አጥ ድጎማ መከልከሉ አግባብነት ያለውና በሕግም የተመሠረተ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።

https://p.dw.com/p/1Dlxr
ምስል www.Finanzfoto.de - Fotolia.com

ወጣቷ ሩሜኒያዊት፤ እ ጎ አ ከ 2010 ዓ ም, አንስቶ ጀርመን ውስጥ በላይፕትዚግ ከተማ የምትኖር ሲሆን ፤ መስተዳድሩ ለአንድ ልጇ ከሚሰጠው የልጅ አበል ውጭ ለሥራ አጦች የሚከፈለውን ገንዘብ ስለከለከላት ፣ ለአውሮፓ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብላ ስትከራከር ከቆየች በኋl ነው ፍርድ ቤቱ፤ የላይፕትዚግ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በማጽናት ሥራ ለሌላቸው ዜጎች የሚሰጠው አበል ባለመብት ልትሆን እንደማትችል የበየነው።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ