1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀለምና ቡሩሽን ለመጀመርያ የጨበጠችዉ የዛሬ አራት ዓመት ነዉ

ሐሙስ፣ ኅዳር 15 2009

ሠዓሊዋ በጀርመን ስትኖር ወደ 20 ዓመታትን ያስቆጠረች ብትሆንም፤ የሥነ-ጥበብ ተሰጥኦዋ ድንገት ብቅ ያለዉ የዛሬ አራት ዓመት ነዉ። ሠዓሊ ሃይማኖት መሰለ እናትም ወጣትም ናት ግን የሥዕል ተሰጦኦን ያገኘችዉ፤ ከመሸ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2T8sR
Bilder der äthiopischen Künstlerin Haimanot Mesele (Haimi Art)
ምስል Haimanot Mesele

ዛሬ ወጣትዋ ሠዓሊ የኢትዮጵያን ባሕላዊ አልባሳት መልክአ ምድር የአሳሳል ዘይቤ በሚያስቃኘዉ የጥበብ ሥራዎችዋ ድልድይን በመዘርጋት፤ ኢትዮጵያን ከጀርመን ከአዉሮጳ ብሎም ከሰሜን አሜሪካ በማገናኘት ባህልዋን ታስተዋዉቃለች።  ታዋቂም ሆናበት ብዙ ተከታዮችን አፍርታለች። 

ሠዓሊ ሃይማኖት መሠለ ትባባለች በጀርመን ስትኖር ሁለት አስርተ ዓመታትን አስቆጥራለች። ስዕል በተሰጥዖ አግኝታዉ በትምህርት አዳብራዉ በትርፍ ጊዜዋ በህብረ-ቀለማት ቡሩሽ ከሸራ እያገናኘች የሃገርዋን ናፍቆት ትወጣ ባህልዋን ታስተዋዉቅ እንጂ ፤ በአስተዳደር ሞያ ተቀጥራ በቀን ለስምንት ሰዓታት የምታገለግለዉ ከስነ ጥበብ ጋር ግንኙነት የሌለዉ ሥራን ነዉ። ቢሆንም ለሥዕል ሥራዎችዋ ግብዓት የሚሆንዋት ስራዎችዋን በአዕምሮዋ የምትስለዉ በአስተዳደር ስራ ላይ ሳለች ነዉ።

Bilder der äthiopischen Künstlerin Haimanot Mesele (Haimi Art)
ምስል Haimanot Mesele

ሃይማኖት የምትስላቸዉ ረቂቅ ሚስጥር አዘል ሥዕሎችዋ ታዋቂነትን እያገኘች ነዉ። 

ምዕራባዉያኑ ረቂቅ ማለት አብስትራክት የሚባል ሥዕልን ነዉ የሚወዱት ማለት ነዉ?

እዚሁ በጀርመን ነዋሪ የሆኑትና የሠዓሊ ሃይማኖት ሥዕሎችን አድናቂ ከሆኑት መካከል ሐረገወይን ጌታቸዉ አንዷ ናቸዉ። ስለ ሥነጥበብ ብዜ እዉቀት የለኝ ብሎም ግን በሠዓሊ ሃይማኖት ላይ ያየሁት ጥበባዊ ስራ ለስዕል ፍቅር እንዲያድርብኝ አድርጎኛል ሲሉ ይገልጻሉ።

Bilder der äthiopischen Künstlerin Haimanot Mesele (Haimi Art)
ምስል Haimanot Mesele

ሠዓሊ ሃይማኖት መሰለ እናትም ወጣትም ናት ግን የስዕል ተሰጦኦን ያገኘችዉ፤ ከመሸ ነዉ። የዛሬ አራት ዓመት ። እንደ ብዙዎች አድናዎችዋ ደግሞ ሥዕልዋን ተመልክተዉ አድንቀዉ ሠዓሊዋ ከልጅነት ጀምሮ ስትተገብረዉ የነበረ ሥራዋ እንደሆን ነዉ የሚያምኑት 

ሠዓሊ ሃይማኖት ሌሊት ስድስት ሰባት ሰዓት ተቀምጣ በመሳል በርካታ ሥዕሎች አጠራቅማ ወደ ኢትዮጵያ ጭና በአደገችበት በሐዋሳ ከተማ የሥዕል አዉደርዕይ አቅርባለች በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ሠዓሊ የሞያ ባልደረቦችን ተዋዉቃ ልምድን በመለዋወጥ መጀመርዋን ተናግራለች ።   

 ሥዕሎችዋን ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ ብዙ ዉጣ ዉረድ እንደገጠማት የምትናገረዉ ሠዓሊ ሃይማኖት መሠለ ፤ ጀርመናዉያን ማንኛዉንም ሥዕል የራስ መሆኑን በማረጋግጫ አይተዉና ፈትሸዉ በይለፍ ከአገር መዉጣት ይችላል ሲሉ ብቻ ፈቃድ እንደሚሰጡ ተናግራለች።

ለቃለ ምልልሱ የተባበሩንን በዶይቼ ቬለ ስም እያመሰገንን ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።    

አዜብ ታደሰ  

ሸዋዬ ለገሠ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ