1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞቃዲሾ እና የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2005

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ዘጠኝ አባላት የነበሩት የአጥፍቶ ጠፊ ቡድን ትናንት በሀገሪቱ ላዕላይ ፍርድ ቤት ላይ በጣለው የፈንጂ ጥቃት ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች፡ በሌላ የቦምብ ጥቃት ደግሞ አምስት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የሶማልያ ፀጥታ ኃይላት

https://p.dw.com/p/18GLT
ምስል Reuters

በወቅቱ በከተማይቱ ዓቢይ የጦር መሣሪያ ክምችት ፍለጋ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። እስካሁን ከ 400 የሚበልጡ ሰዎች ከትናንቱ ጥቃት ጋ በተያያዘ ተጠርጥረው መታስራቸውን ከፍተኛ የፖሊስ ባለሥልጣን መሀመድ ሀሰን ገልጸዋል። ካሁን ቀደም በሶማልያ የፀጥታ ኃይላት ተገድጄ ተደፈርኩ ባለች ሴትና ስለዚሁ ክስ በዘገበዉ ጋዜጠኛ ላይ እሥራት የተበየነውን የአንድ ዓመት እሥራት በሻረው ፍርድ ቤት ለተጣለው ጥቃት አሸባብ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን፡ ፍርድ ቤቱ የጥቃቱ ዒላማ የሆነው ክሱ ከተሻረበት ድርጊት ጋ የተያያዘ መሆኑን በለንደን የመካከለኛ ምሥራቅ እና የአፍሪቃ ልማት ጥናት ተቋም መምህር የሆኑት ላውራ ሀሞንድ አስረድተዋል።
« ፍርድ ቤቱ የጥቃት ዒላማ የሆነው አሸባብ በፍትሑ አውታር ተሀድሶ እንዲደረግ እንደማይፈልግ ለማሳየት ነው። እንደሚታወቀው፡ ተገዳ ተደፈረች የተባለችውን ሴት ክስ በቅርብ የተከታተሉት ሁለቱ ዳኞች በአስከፊው የሣምንቱ መጨረሻ ጥቃት ተገድለዋል። »
በሣምንቱ መጨረሻ የፈንጂ ጥቃት በርካቶች ከተገደሉና የመዲናይቱ ፀጥታ ገና አስተማማኝ እንዳልሆነ ከታየ በኋላ የአሸባብ አባላት ተጨማሪ ጥቃት እንደሚጥሉ ዝተዋል።

Somalia Mogadischu Anschlag ARCHIVBILD MÄRZ 2013
ምስል Mohamed Abdiwahab/AFP/Getty Images

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ