ሞስኮ-ሩሲያ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ነቀፈች
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008ማስታወቂያ
የሩሲያ አትሌሎች በመንግሥት ድጋፍ ሐይል ሰጪ ንጥረ-ነገር ይወስዳሉ በማለት በዉድድሩ እንዳይካፈሉ የዓለም ፓራሊምፒክስ ኮሚቴ (IPC) ከሁለት ሳምንት በፊት ወስኖ ነበር።ዉሳኔዉን በመቃወም ሩሲያ ይግባኝ የጠየቀችበት ፍርድ ቤት ዛሬ ይግባኙን ዉድቅ አድርጎ የ IPCን ዉሳኔ እንዲፀና በይኗል።የሩሲያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በመላዉ አካል ጉዳተኞች ላይ የተቃጣ ወንጀል በማለት አዉግዘዉታል።ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለዉ እንዳሉት የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ 80 በመቶ ፖለቲካን፤ 20 በመቶ ደግሞ ሐይል ሰጪ ንጥረ ነገርን መሠረት ያደረገ ነዉ።በዚሕ ዉሳኔ መሠረት ከ250 የሚበልጡ የሩሲያ አካል ጉዳተኛ አትሌቶች ጳጉሜ ማብቂያ በሚጀመረዉ ዉድድር ላይ አይካፈሉም።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ