ሞሮኮ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ድሬዳዋ ውስጥ የማዳበሪያ ፋብሪካ ልትገነባ ነው
ቅዳሜ፣ ኅዳር 10 2009ማስታወቂያ
የዓለም ግዙፉ የፎስፌት ማዕድን ላኪ የሞሮኮ ኩባንያ (OCP) የማዳበሪያ ማምረቻ ኢትዮጵያ ውስጥ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረመው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መኾኑም ተገልጧል። የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካው የሚገነባው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ እንደሆነም ተዘግቧል። ሞሮኮ ዘርፈ-ብዙ በኾኑ የትብብር መስኮች የተለያዩ ውሎችን ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረሟን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከው ዘገባ ይጠቁማል። የሞሮኮ ንጉሥ 6ኛው በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ2 ቀናት ጉብኝት አጠናቀዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ