ሞምባሳ ውስጥ የተገደሉት መንፈሳዊ መሪ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 23 2004አመፅ የሚያስነሱት ካላቆሙምም ጠንካራ ርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል። ለሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅት ሁማን ራይትስ ዎች በጉዳይ ላይ ያለውን ፤ ልደት አበበ እንደሚከተለው አሰባስባለች።
« አገሪቷን በጉልበተኛ ስርዓት አመራር ልናራምድ አንችልም ነው ያሉት፤ የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ። አክለውም ግድያን ፍፁም አንፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል። ሼክ አቦድ ሮጎ መሐመድ ያለፈው ሰኞ ባልታወቀ ሰው ከተገደሉ በኋላ ሞምባሳ ገና ዛሬ ነው የተረጋጋችው። የሁማን ራይትስ ዎች የምስራቅ አፍሪቃ ጉዳይ ተመራማሪ ቤን ሮውሌንስ እንደሚሉት፤ ጉዳዩ አሳሳቢ ነው።
« ማንም ይሁን ማን ድርጊቱን የፈፀመው አንዳንድ በነዚህ ሰዎች የተቆጡ ራሳቸውን በትጋት የሚከላከሉ ኬንያውያንም ይሁኑ የኬንያ ባልስልጣናት ድብቅ ኃይል በጉዳዩ ለመጨነቅ በቂ ምክንያት አላቸው።»
ከቤተሰባቸው ጋ ከሞምባሳ ወደ ማሊንዲ ሲጓዙ በጥይት ተመተው የተገደሉት መንፈሳዊ መሪ፤ ከአሸባብ ቡድን ጋ ግንኙነት አላቸው ተብሎ ይገመታል። ለቡድኑም ሶማሊያ ውስጥ ገንዘብ እና ተዋጊዎች አቅርበዋል በማለት ይተቻሉ። ዩናይትድ እስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሸባሪነት እቀባ ከተደረገባቸው ስም ዝርዝር ውስጥ ከተዋቸዋል። በርግጥ ከግድያው በስተጀርባ ስላለው ሰው እስካሁን የኬንያ መንግስትም ይሁን የሰው መብት ተሟጋጅ ድርጅቶች አልደረሱበትም። እንደ ኬንያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጠባባቂ ምክትል ዋና ፀሀፊ ፤ በርንናርድ ሞጌሳ ገለፃ፤ ከሆነ የመንፈሳዊው መሪ ሼክ አቦድ ሮቦ መሐመድ የተገደሉት በፖሊስ ድክመት ነው።
« ህይወታቸው በአደጋ ላይ እንደሚገኝ አንድ ዘገባ እንኳን ከወጣ የፖሊስ ኃላፊነት ነበር ምን አይነት ሰው ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚችል። ይህ የፖሊስ ቸልተኝነት ነው ማለት እችላለሁ። ወቀሳቸው በጥሞና አልተደመጠላቸውም። አንዳንድ ከለላ አልተሰጣቸውም።»
የመንፈሳዊ መሪው ደጋፊዎች ባስነሱት አመፅ ቤተ ክርስትያናት እና መኪናዎች በእሳት ተለኩሰዋል። ሱቆች መዝብረዋል። እንደ BBC ዘገባ ደግሞ አብያተ-ክርስቲያን ይህንን ድርጊት ለመቃወም ያደረጉትን ጥሪ ግጭቱን ይበልጥ ላለማጠናከር በሚል ሰርዘውታል። የኬንያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጠባባቂ ምክትል ዋና ፀሀፊ ፤ ሞጌሳ ወደፊትም
እንደዚህ አይነት ድርጊቶችን ለመከላከል እንደ መፍትሄ የሚያዩትን ሲገልፁ፤
« ሁለት መፈፀም ያለብን ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው ያካባቢው ባለስልጣናት ስለአካባቢው ሰላም አንስተው መወያየት ይኖርባቸዋል። ሁለተኛ ፖሊስ ከወንጀል ጋ የተያያዙ ድርጊቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማሳየት አለበት። ሰዎች በፖሊስ አቅም መተማመን እንዲችሉ።»
በአቦድ ሮጎ ግድያ እስካሁን በቁጥጥር ጥር የዋለ አካል የለም። እንደ «ደይሊ ኔሽን» ዘገባ ከሆነ የመንፈሳዊ መሪው ደጋፊዎች ባስነሱት አመፅ 20 የሚደርሱ ሰዎች ታስረዋል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ