1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምኒሊክን የዘከረዉ የዉርሰ ኢትዮጵያ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 7 2006

ዉርሰ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት ሰሞኑን በጀርመኗ ታሪካዊት ከተማ ጎታ 16ኛዉን ዓመታዊ ጉባኤዉን አካሂዷል። ጎታ ኢትዮጵያዉ አባ ጎርጎርዮስና ጀርመናዊዉን ሂዮብ ሉዶልፍን ከሶስት መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ያስተናገደች ከተማ ናት።

https://p.dw.com/p/1A1iQ
ምስል DW

ሁለቱ የታሪክ ሰዎች በተስተናገዱበት የቤተመንግስት መስታወት አዳራሽ ዉስጥ ዘንድሮ የተካሄደዉ የዉርሰ ኢትዮጵያ ጉባኤ ደግሞ በአጼ ምኒሊክ ሥራና ታሪክ ላይ ተወያይቷል። ጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የከተማዋ ከንቲባና የድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበር ልጅ ዶክተር አስፋወሰን አስራም ስለእህት ከተማ ጉዳይ እንዲታሰብበት መጠቆማቸዉን በስብሰባዉ የተካፈለዉ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል በላከዉ ዘገባ አመልክቷል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያምተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ