ምርጫ በናይጀሪያ
ቅዳሜ፣ መጋቢት 24 2003ማስታወቂያ
እአአ የፊታችን ሚያዝያ ዘጠኝ አዲስ ፕሬዚደንት ይመርጣሉ። ናይጀሪያ ውስጥ እአአ በ 1999ዓም ስርዓተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገና ከተተከለ ወዲህ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሲደረግ ያሁኑ ሶስተኛ ይሆናል። አስመራጩ ኮሚስዮን ባለፉት ሁለት ምርጫዎች አንጻር ያሁኑን ምርጫ ሂደት ትክክለኛ እና ግልጽ ለማድረግ አቅዶዋል። ሀቀኛው ስርዓተ ዴሞክራሲ ለናይጀሪያ የኤኮኖሚውን ዕድገት እንደሚያስገኝላት ዜጎችዋ ብቻ ሳይሆኑ የውጭው ዓለም ተስፋ አድርጎዋል።