እናም በአምስት ደረጃ ምርጫዉ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል። በዓለም ላይ ትልቋ የዴሞክራሲ አገር በምትባለዉ ህንድ ታዲያ የምርጫ ሂደቱ አንድ ወር ይፈጃል ተብሏል። ትናንት የመጀመሪያዉ ደረጃ አልፏል። ሆኖም ግጭትና ጉዳት ደርሷል፤ ሰዎች ሞተዋል፤ ፖሊሶችም ቆስለዋል። ከደፈረሰዉ ጸጥታ ጀርባ የማኦ ተከታዮችና አክራሪ ሙስሊሞች እንዲሁም ተስፈንጣሪ ቡድኖች እንዳሉበት በብዙዎች ዘንድ ተገምቷል።
ይልማ ኃይለሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ