ሜዲቴራንያን ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ አውሮፕላን
ሰኞ፣ ጥር 17 2002የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ዋቄ ዛሬ እንደተናገሩት አስራ አራት አባላት የሚገኙበት የአየር መንገዱ አጣሪ ቡድን ወደ ቤይሩት ሄዷል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚለው ትናንት ለሊት የተከሰከሰው ቦይንግ 730-800 አውሮፕላን አየር መንገዱ ኤሮ ስፔስ ከተባለው ድርጅት ተከራይቶ የሚገለገልበት አውሮፕላን ነው ።
አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያዉ አዉሮፕላን ለገጠመዉ ችግር ምክንያት የሆነዉ ምንድ ነዉ የሚለዉ እስካሁን እየተጣራ ያለ ጉዳይ ነዉ። አደጋዉ ከሽብር ጋ ግንኙነት እንደሌለዉ ከልባኖስና ኢትዮጵያ መንግስታት ተነግሯል። አዉሮፕላኑ አየር ሆኖ ለአራት ተከፋፍሎ ባህር ላይ መከስከሱ ነዉ የሚገለጸዉ።ከአፍሪቃ አየር መንገደች አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት እና ወደ ሀምሳ ስድስት አገራት በመብረር በአንጋፋነቱ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም ከፍተኛ ተወዳዳሪዎች ከሚባሉት አየር መንገዶች ተርታ ይሰለፋል ።
በትርፋማነቱ የሚታወቀው ይኽው አየር መንገድ በበራ ዋስትናው ዝና ካተረፉ አየር መንገዶች ጋር ይጠቀሳል ። አየር መንገዱ በእስከዛሬ ታሪኩ የአሁኑን ሳይጨምር እ.ጎ.አ ከ 1980 በኃላ ሁለት አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋዎች ናቸው የደረሱበት ።
ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ የወጡ መግለጫዎችን ተከታትሏል
ሸዋ ለገሰ ወደቤይሩት ደዉላ ዘገባ አጠናቅራለች።
ጌታቸው ተድላ የአየር መንገዱን የአደጋ ታሪክ ተመልክቷል
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ