1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማይክሮ-ክሬዲት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ኅዳር 13 2004

በዓለም ላይ ከአንዲት ዶላር ባነሰች የዕለት ገቢ ኑሮውን የሚገፋው ድሃ ሕዝብ ዛሬ ከሚሊያርድ ይበልጣል። ድህነቱ በአብዛኛው ተጭኖ የሚገኘው ደግሞ በሴቶች ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/Rxs8

ሁኔታውን ለመለወጥ አነስተኛ ብድር፤ ማለት ማይክሮ-ክሬዲት በመስጠት በእሢያ፣ በአፍሪቃና በላቲን አሜሪካ ጥረት ከተጀመረ ወዲህ የተወሰኑ ዓመታት ቢሆኑትም ሴቶችን በኤኮኖሚ አቅም ማጠናከሩ በወቅቱ ገና ብዙ ጉዞ የሚቀረው ነው የሚመስለው።

ባለፈው ሣምንት አምሥተኛው ዓለምአቀፍ የማይክሮ-ክሬዲት ዓቢይ ጉባዔ ስፓኝ ከተማ ቫላዶሊድ ላይ ተካሂዶ ያለፈውን ጊዜ ሂደት መለስ ብሎ ለማጤን ሞክሮ ነበር። በጉባዔው ላይ ከሺህ የሚበልጡ ከአንድ መቶ ሃገራት የተጓዙ ልዑካን ሲሳተፉ አራት ቀናት የፈጀው ስብሰባ በተለይም አንዳንድ አበዳሪዎች የሚጠይቁት ከፍተኛ ወለድ በተገልጋዮች ላይ ባስከተለው የዕዳ ችግር የተነሣ ብዙ ሲያከራክር ታይቷል።
ስብሰባው በተለይም በአንዳንድ በሕንድና በሜክሢኮ በሚገኙ የማይክሮ-ፊናንስ፤ አነስተኛ ብድር አቅራቢ ተቋማት ላይ ሂስ ሲሰነዝር ጉዳዩ እንዳይደገም መቆጣጠሪያ ዘዴ የመስፈኑን አስፈላጊነት ደጋግሞ ነው የተነሣው። የኦክስፋም ግብረ-ሰናይ ድርጅት ዓለምአቀፍ አማካሪ ሊንዳ ማዮክስ ዛሬ ከለንደን በስልክ እንደገለጹልኝ ከሆነ በጉባዔው ላይ ያንያህል የረባ ዕርምጃ ለማድረግ አልተቻለም።

“በጉዳዩ ብዙ ውይይት ተካሂዷል። በተለይ በአጠቃላይ የሴቶችን የገንዘብ አግባብ በማጠናከሩ ረገድ! ግን ለሴቶች በኤኮኖሚ መጠናከር የሚያመች ይህ ነው የሚባል ራዕይ እስካሁን ገሀድ አልሆነም። ሁሉም ነገር መሠረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላቱን ምርትን በመሸጡ የተወሰነ ነው። እንግዲህ የተለያዩት ድርጅቶች ወደፊት የሚያተኩሩበት ብዙ ነገር ይኖራል”

በኢትዮጵያ ላይ እናተኩርና የማይክሮ-ፋይናንስ ተገልጋይ ሴቶች ቁጥር ባለፉት ዓመታት እየጨመረ ነው የመጣው። በዚሁ መለስተኛ ብድር ለመቋቋም የሚጥሩትን ሴቶች ከሚንከባከቡት መካከል አንዱ “ራስ-አገዝ የሴቶች ድርጅት” በእንግሊዝኛው አሕጽሮት WISE የተሰኘው ሲሆን የማሕበሩን ዳይሬክተር ወሮ/ጽጌ ሃይሌን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታና በማሕበሩ ዕርምጃ ላይ አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ሂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ