ኦዲንጋ በድጋሚ ምርጫ «ላልሳተፍ እችላለሁ» እያሉ ነው
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2009ማስታወቂያ
አዲንጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫው ዕለትም እንዲቀየር ከመጠየቃቸው ጎን እስከምርጫው ዕለት ይሟሉ ያሏቸው በርካታ ጥያቄዎች ማቅረባቸው ተሰምቷል።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ60 ቀናት ውስጥ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ዓርብ መወሰኑን ተከትሎ የሀገሪቱ የምርጫ እና ድንበር ኮሚሽን የድምጽ መስጫው ቀን ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም እንዲሆን ትላንት ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ ኦዲንጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የምርጫው ዕለት በጥቅምት 14 አሊያም በጥቅምት 21 እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ በድጋሚ ምርጫው ለመሳተፍ መሟላት አለባቸው ያሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎችም ዘርዝረዋል፡፡ ከቅድመ ሁኔታዎቹ ውስጥም የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ስድስት ኃላፊዎች ከስልጣናቸው እንዲነሱ የጠየቁበት ይገኛል፡፡
በኬንያ ድጋሚ ይደረጋል የተባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫን በተመለከተ የተቃዋሚው ወገን ስለያዘው አቋም ናይሮቢ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረማርያም መኮንንን አነጋግረናቸዋል።
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ