1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማብቂያ ያጣዉ የስደተኞች እልቂት በሜዲተራንያን

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2008

የስደተኞች ስቃይ ዋይታና ሞት ዛሬም በአዉሮጳ ምሥራቃዊና ደቡባዊ ድንበሮች እየተሰማ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት ብቻ ከሊቢያ የባህር ጠረፍ ሜዲተራንያንን ባህር አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ከሞከሩት በሺ ከሚቆጠሩት ስደተኞች ዉስጥ ከ 900 በላይ የሆኑት የዉኃ እራት ሆነዉ መቅረታቸዉ በአደባባይ ተገልጾአል።

https://p.dw.com/p/1IxkR
Mittelmeer Libyen Flüchtlingsboot Rettungsaktion
ምስል Reuters/Marina Militare

ማብቂያ ያጣዉ የስደተኞች እልቂት በሜዲተራንያን


እነዚህ በብዛት ከአፍሪቃ ሃገራት እንደመጡ የሚነገርላቸዉ ስደተኞች ሩቅ አስበዉ በአጭር የተቀጩት ወጣቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጭምር በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ይቀዝፉበት የነበረዉ ጀልባ ተገልብጦ ፤ ተሰብሮ አልያም ተበላሽቶ መሆኑ ከመገለፁ ዉጭ አስክሬን እንኳ የተገኘዉ የጥቂቶች ብቻ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። ይህ የሆነዉ የዛሬ ሦስት ዓመት በዚያዉ በሜዲተራንያን ባሕር ላይ በኢጣልያ የላምፔዱዛ ደሴት አካባቢ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ከሞቱ በኋላ የአውሮጳ ህብረት ተመሳሳይ አደጋ እንዳይፈጠር በርካታ ርምጃዎችን መውሰዱን እና የነፍስ አድን ግብረ ኃይልንም ማቋቋሙን በገለጸ ማግስት ነዉ። በዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅት ማብቂያ ያጣውን የስደተኞች ስቃይና እልቂት ከአዉሮጳ የስደተኞች ፖሊስ ስምረትና ጉድለት ጋር እያነጻጸርን እናያለን።



ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ