1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማሕደረ-ዜና የ «መሬት ቅርምት» ና ኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ጥር 3 2002

የ«መሬት ቅርምት» ወይም «Land Grab» (እንደ እንግሊዘኛዉ) የተሰኘዉ ሥልት ከሚጠቅም ወይም በተቃራኒዉ ከሚጎዳቸዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት

https://p.dw.com/p/LQgi
ምስል AP

የ«መሬት ቅርምት» ና ኢትዮጵያ

የ«መሬት ቅርምት» ወይም «Land Grab» (እንደ እንግሊዘኛዉ) የተሰኘዉ ሥልት ከሚጠቅም ወይም በተቃራኒዉ ከሚጎዳቸዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።የኢትዮጵያ መንግሥት ለዉጪ ባለሐብቶች ሥለሚያኮናትረዉ መሬት ግልፅ መርሕ (ፖሊሲ) የለዉም፥ መሬት ማኮናተር ሳይሆን ሐገር መሸጥ ነዉ፥ለቅኝ ገዢዎች ማጋለጥ ነዉ፥ ወዘተ የሚሉ ወቀሳና ትችቶች እየተዥጎደጎዱበት ነዉ።የዚያኑ ያክል መርሁ ምርታማነትን የሚያሳድግ፥ ረሐብን ለመከላከል የሚረዳና የሥራ እድል የሚፈጥር ነዉ ባዮችም አሉ ።በዛሬዉ ዝግጅታችን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሠ እንግዳዉ ጉዳዩን በደምሳሳዉ ለመቃኘት ይሞክራል እነሆ፥

ታደሰ እንግዳው

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ