ሙባረክና የግብፅ አብዮት
ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2004ማስታወቂያ
ግብፅ ሁለት በሽተኞችዋን እያስታመመች ነዉ።የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ሆስኒ ሙባረክን-እና የሙባረክን የሰላሳ ዘመን አገዛዝ ያስወገደዉን ሕዝባዊ አብዮት።የሠማንያ አራት አመቱ የቀድሞ አምባገነን ገዢ ሆስኒ ማበረክ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ እያጣጣሩ ነዉ።ሙባረክን አምና የካቲት ከሥልጣን ያስወገደዉ የግብፅ ሕዝባዊ አብዮትም ሙባረክን በተኩት የጦር መኮንኖች ሕልቅቱ ተይዞ በመኖር አለመኖር መሐል እያቃሰተ ነዉ።የሙባረክን ጤንነት፥ የግብፅን ፖለቲካዊ እዉነት በተመለከተ ከጂዳዉ ወኪላችን ከነቢዩ ሲራክ ጋር አጭር ዉይይት አድርገናል።እነሆ።
ነብዩ ሲራክ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ