1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙስና በአውሮፓና በጀርመን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004

በየሃገራት ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በመባል የሚታወቀው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ ችግሩ በአንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት ስር የሰደደ መሆኑን ጠቁሟል ። በጀርመንም መስተካከል

https://p.dw.com/p/15Cjy
Close-up handcuffs and money over white background. Not isolated. Close-up handcuffs and money © S-Christina #26609805
ምስል Fotolia/S-Christina

በየሃገራት ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በመባል የሚታወቀው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ ችግሩ በአንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት ስር የሰደደ መሆኑን ጠቁሟል ። በጀርመንም መስተካከል ያለባቸው አሠራሮች መኖሩን ጠቁሟል የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው አብራችሁን ቆዩ ።
በአብዛኛው የታዳጊው ዓለም ችግር ብቻ ተደርጎ የሚታየው ሙስና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሚያራምዱ ምዕራብውያን ሃገራትም ሊጠፋ ያልቻለ አሁንም መፍትሄ የሚፈልግለት አንድ ችግር ነው ። ጀርመን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች ፖለቲከኞች ጭምር በሙስና ቅሌት ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም ። በዚህ ዓመት እንኳን የቀድሞው የጀርመን ርዕሰ ብሄር ክርስያን ቩልፍ ከብዙ ትችና ውጣ ውረድ በኋላ ሥልጣናቸውን እስከመልቀቅ የደረሱበት ሁኔታ ከሙስና ተለይቶ
የማይታይ እንዳልሆነ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲያነሱ ሲጥሉት የከረሙት ጉዳይ ነው ። በቅርቡ የጀርመን የልማት ሚኒስትር ዲርክ ኒብል አፍጋኒስታን ለሥራ በሄዱበት አጋጣሚ የገዙትን ምንጣፍ በመንግሥት ወጪ ጀርመን ማስመጣቸውና ቀረጥም ሳይከፍሉ ማስገባታቸው እንዲሁ ከአንድ ሚኒስትር የማይጠበቅ ድርጊት መሆኑ እየተወሳ ከሰሞኑ አንዱ የመነጋገሪያ አርዕስት  ለመሆን በቅቷል ።

Deutschland Geschäftsführer von Transparency International Christian Humborg
ክርስቲያን ሁምቦርግምስል picture-alliance/dpa

በጀርመንም ሆነ በሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ከሚሰጥ እርዳታና ድጎማ ጋር ተያያዘው የሚከሰቱና ሊከሰቱ የሚችሉ ሙስናዎችም አነጋጋሪ ናቸው ። በዚህ ሰበብ የሚከተል ሙስና የሚገታበት መንገድ ሥራ ላይ እንዲውል ዓለም ዓቀፉ የፀረ ሙስና ድርጅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ረቡዕ ባወጣው ዘገባ አሳስቧል ።
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በአውሮፓ ሙስና ያለበትን ደረጃ መዘዞቹንና መሻሻል ያለባቸውን አሠራሮች የጠቆመው በ25 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገሮች ፍተሻ ካካሄደ በኋላ ነው ። በድርጅቱ መመዘኛ 3 የአውሮፓ ሃገሮች ከሁሉም በጣም የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሙስናን መከላከል የሚያስችል አሠራር ዘርግተዋል ። እነርሱም ዴንማርክ ኖርዌይ ና ስዊድን ናቸው ።  እንደ ድርጅቱ ግምገማ በነዚህ ሃገሮች  የህዝብ ዓይንና ጆሮ የሆኑ ብርቱ የመብት ተከራካሪዎች ፣ ጠንካራ የሂሳብ መርማሪዎችና ተቆጣጣሪዎች አሉ ፤ የፍትህ ስርዓታቸውም ሆነ ህግ አስፈፃሚዎቻቸው በአግባቡ ሥራቸውን ይወጣሉ ።
  ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የንግድና የኤኮኖሚ ተጠሪዎችን በማነጋገር ባካሄደው ግምገማ መሰረት ጀርመንን ከ 183 ሃገራት 14 ተኛ ደረጃ ላይ ነው ያስቀመጠው ። ድርጅቱ በአሁኑ ግምገማው በ25 የአውሮፓ ሃገራት ምን ያህል ሃቀኛ አሰራሮች እንዳሉና በትክክልም እየተተገበሩ መሆን አለመሆናቸውን በተመለከተ ከሌሎቹ ጊዜያት በተለየ ጠለቅ ያለ ምርመራ ማካሄዱን ነው ያስታወቀው ። በዚህ ተግባሩም በአውሮፓ ግልፅ አሠራርን ለመተግበር በሚደረገው ጥረት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መፈተሽ ነበር ዋነኛ ዓላማው ። በድርጅቱ ግምገማም ጀርመን ሃቀኛ አሰራርን ገቢራዊ በማድረግ በኩል ከጥሩ እስከ በጣም ጥሩ የሚደርስ ደረጃ አግኝታለች ። ይሁንና የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ቢሮ ሃላፊ ክርስቲያን ሁምቦርግ እንዳሉት ከጀርመን የተሻለ ደረጃ ያገኙ ሌሎች የአውሮፓ ሃገራትም አሉ ።    


። ጀርመን በመመዘኛ መሠረት ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ በሚያሰኝ ህቀኛ የአሰራር ስርዓት ትወድሳለች ። ስርዓት ያለው ሃቀኛ ስርዓት የዘረጋች ናት ስለዚህ ጉዳይ ማንም ካለው ውጭ ሊል ወይም መጥፎ ነገር ሊታይ አይገባም ። ነገር ግን በተወሰነ ደረጃ ቢሆን ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ልዩነት አለ ። የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙትም ስካንድኔቭያኑ ዴንማርክና ስዊድንን የመሳሰሉት ሃገራት ናቸው ። »
አውሮፓ ከዓለም ሙስና እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ደረጃ ላይ የሚገኝበት ክፍለ ዓለም ተደርጎ ቢታይም የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ግን ችግሮች መኖራቸውንና አዝማሚያቸውም አደገኛ መሆኑን ነው የጠቆመው ። እንደ ድርጅቱ በአውሮፓ በተለይም በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው ወደ ሜዲቴራንያን ባህር በሚጠጉት ሃገራት ከፖለቲካና ከንግድ ጋር የተገናኘ ደረጃው ከፍ ያለ ሙስና አለ ። ይህም እንደ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የዩሮ ቀውስ ካስከተለው መዘዝ ለመውጣት የሚታገሉትን የነዚህን ሃገራት ለአደጋ የተጋለጠ ኤኮኖሚ ይበልጥ ሊያዳክም ይችላል ። የበጀት ጉድለትና የእዳ ክምችት ዋነኛው መንስኤው የሆነው የዩሮ ቀውስ ወደ 2 ዓመት ተኩል የሚጠጋ እድሜ አስቆጥሯል ። በዚህ ምክንያትም የወጪ እጥረት በጋጠመበት ፣ መንግሥት ያስገባ የነበረው የሥራ ግብር በሥራ አጥ ቁጥር መጨመር ሰበብ በቀነሰበት በነዚህ ሃገራት በዚህ ወቅት ላይ ይላል ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሙስና ሲታከልበት የህዝብ ሃብት ብክነት አያጠያይቅም ።

Symbolbild Korruption Euro Scheine und Hände
ምስል picture-alliance/ dpa


ሙዚቃ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,በድርጅቱ ፍተሻ መሠረት ብዙውን ጊዜ በእዳ የሚዘፈቁት ደካማ ፀረ ሙስና አሠራር የዘረጉ ሃገራት ናቸው ። እንደ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በነዚህ ሃገራት የሂሳብ ተቆጣጣሪ ቷቋማት ደካማ ሲሆኑ ብዙውን ጊዜም ከመንግሥት ነፃ አይደሉም ። ዘገባው ችግሩ ጎልቶ የሚታይባቸው ሲል የጠቀሳቸው ሃገሮች ግሪክ ኢጣልያ ፖርቱጋል ና ስፓኝ ናቸው ። እነዚህ አራት ሃገሮችም  ከዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ነው የሚገኙት ። ድርጅት በዘገባው እንዳለው ሃገራቱ በህዝብ አስተዳደር ዘርፍ ስር የሰደደ ችግር የሚገኝባቸው ሲሆን ባለሥልጣናትም ለድርጊታቸው ተጠያቂ የሚሆኑባቸው ሃገራት አይደሉም ። በተጠቀሱት ሃገራት ፖለቲከኞች እና የንግድ ድርጅቶች መሪዎች የሥራ ውሎችን ለማሸነፍ ና አንዳንድ መርሆችም ተቀባይነት እንዳያገኙ ለማደርግ ሥልጣናቸውንና ኃይላቸውን በመጠቀም ተፅዕኖ ያደርጋሉ ። የህዝብ እንደራሴዎችም ቢሆኑ ብዙውን ጊዜ የፀረ ሙስና ህጎችም ሆነ ሌሎች ደንቦች ተግባራዊ ማደርግ ይሳናቸዋል ። እናም ይላል ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሙስናና በነዚህ ሃገራት አሁን የተከሰተው የገንዘብና የበጀት ቀውስ ትስስር ሊናቅ የሚገባ አይደለም በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሙስና ምክንያት በዓመት ወደ 120 ቢሊዮን ዩሮ ማለትም ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚባክን ያስረዳል ። ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል እንደሚያክለው የመንግሥት ይዞታዎችን ወደ ግል በማዛውር ሂደት ለየሃገራት የሚሰጡ የገንዘብ ድጎማዎች ወደ ግለሰቦች ኪስ የሚገቡባቸው አጋጣሚዎች አሉ ። በዚህ ረገድ ድርጅቱ እንደጠቀሰው በፖርቱጋልና በግሪክ ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት የሚተላለፉባቸው መርሃ ግብሮች ለሙስና አደጋ የተጋለጡ ናቸው ። እንደ ድርጅቱ በዚህ አሠራር ከህዝቡ ይልቅ ወደ ግል ባለሃብቶቹ የተጠጉት ጥቂቶች ብቻ ነው ተጠቃሚ የሚሆኑት ፤ ሃገራቱም የተበደሩትን ገንዘብ የመክፈልና

Transparency International Logo
Bestechung © fovito #20543019
ምስል fovito/Fotolia

በጀታቸውንም የማስተካከል አቅማቸውን ዝቀትኛ ነው የሚሆነው ። ።  በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሙስና ምክንያት በዓመት ወደ 120 ቢሊዮን ዩሮ ማለትም ወደ 150 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚባክን ያስረዳል ። ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ደግሞ የመንግሥት ይዞታዎችን ወደ ግል በማዛውር ሂደት ለየሃገራት የሚሰጡ የገንዘብ ድጎማዎች ወደ ግለሰቦች ኪስ የሚገቡባቸው አጋጣሚዎች አሉ ። በዚህ ረገድ ድርጅቱ እንደጠቀሰው በፖርቱጋልና በግሪክ ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት የሚተላለፉባቸው መርሃ ግብሮች ለሙስና አደጋ የተጋለጡ ናቸው ። እንደ ድርጅቱ በዚህ አሠራር ከህዝቡ ይልቅ ወደ ግል ባለሃብቶቹ የተጠጉት ጥቂቶች ብቻ ነው ተጠቃሚ የሚሆኑት ፤ ሃገራቱም የተበደሩትን ገንዘብ የመክፈልና በጀታቸውንም የማስተካከል አቅማቸውን ዝቀትኛ ነው የሚሆነው ።
በድርጅቱ ምዘና ጀርመን በንግዱና በኢኮኖሚው ዓለም እንዲሁም በዜጎችና በፖለቲካ ግንኙነት ውስጥ ግልፅና ትክክለኛ አሠራርን እየተከተለች ነው ። ያም ሲባል ግን በጀርመን ሁሉም ፍፁም ትክክለኛ አሥራር ነው ማለት አይደለም ።  በትራንስፓረንሲ አስተያየት በበርካታ መስኮች ሊስተካከሉ የሚገባቸው አሰራሮች አሉ ። ለጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ሙስና ውስጥ መዘፈቅም ሆነ ጉቦ መቀበል ህገ ወጥ ነው ። በምርጫ ወቅትም ቢሆን ገንዘብ እየሰጡ ድምፅ መግዛትም እንዲሁ ያስቀጣል ። ሆኖም ይላል ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ጀርመን እጎአ በ2005 ሙስናን ለመከላከል የተለያዩ መንገዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ጥሪ የሚያደርገውን የተባበሩት መንግሥታት ስምምነት አላፀደቀችም ። ይህ ዓለም ዓቀፍ ስምምነት ደግሞ ለ3ተኛ ወገን ቃል መግባትንም ሆነ ይህንኑ አካል ለመጥቀም መስማማትን ህገ ወጥ ያደርጋል ። ተቃዋሚው የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ በዓለም ዓቀፉ ስምምነት ተፅዕኖ ሥር የሚወድቁ ህጎችን ለማሻሻል የሚያስችል ህግ አርቋል ። ጥምሩ መንግሥት ግን ህጉን ለመቀየር እያቅማማ ነው ።

Logo International Aid Transparency Initiative

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ቅርንጫፍ ሃላፊ ክርስቲያን ሁምቦርግ ጀርመን ስምምነቱን አለማፀደቋ ያስገምታታል ይላሉ ። ሌሎች ሃገራት ሙስናን እንዲዋጉ ጥሪ የምታደርገው ጀርመን የተባበሩት መንግሥታትን የፀረ ሙስና ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ አለመቻልዋ ሁምቦርግ እንደሚሉት አሳፋሪ ነው ።
« ሌሎች ሃገሮች በሙስና ላይ ብርቱ እርምጃ መውሰድ ይገባቸዋል ብለን መመሪያ መስጠት የምንፈልግ ከሆነ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ራሳችንን መሳለቂያ ነው የምናደርግ ። የሃገራችን ሴቶችና ወንዶች የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት የተባበሩት መንግሥታት የፀረ ሙስና ስምምነት የሚጠይቀውን ለማጽደቅ ዝግጁ አይደሉም ። ስለሆነም የህዝብ እንደራሴዎች ጉቦ መቀበል የሚያሰጠውን ቅጣት እንዲያጠብቁት እንጠይቃለን ። ሁኔታው በዚህ ሊቀጥል አይችልም የሚሉ ድምጾች እየበረከቱ መጥተዋል ።ከጌዜ ወደ ጊዜ ሥልጣን የያዘው መንግሥት የህዝብ እንደራሴዎች ስምምነቱ እንዳይፀድቅ ይከላከላሉ ።ይሁንና በዚህ አቋማቸው ፀንተው ሊቀጥሉ አይችሉም ። »   
በሁምቦርግ እምነት የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ስምምነቱን ከማፅደቅ ውጭ ሌላ ምርጫ አይኖረውም ። ጀርመን የሚትተችበት ሌላው አንዱ ጉዳይ ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ እርዳታ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ እንዲሆን በማያስገድደው የገንዘብ መጠን ገደብ ነው ።እስካሁን ፀንቶ በቆየው የጀርመን ህግ የህዝብ እንደራሴዎች ለፓርቲ ተብሎ በቀጥታ የሚሰጣቸውን ገንዘብ ይፋ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ከ10 ሺህ ዩሮ ወይም ከ 12 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ ብቻ ነው ። እንደ ሁምቦርግ ይህ የገንዝበ መጠን ብዙ ነው ። ይሄ ገንዘብ ለህዝብ እንደራሴዎቹ ሲሰጥ ለዚያ ውለታ የመክፈል ፈተና

ሊያጋጥማቸው እንደሚችል በቀላሉ መገመት ይችላል ሲሉ ነው ሁምቦርግ አስተያየታቸውን የሰጡት ። ሁምቦርግ ባቀረቡት ሃሳብ መሠረት ይበልጥ ግልፅነት እንዲኖር ጠቃሚው መሣሪያ ድጋፍ ለመሰብሰብ የሚካሄዱ የማባባያ እንቅስቃሴዎች በብሔራዊ ደረጃ በህግ እንዲመዘገቡ ማድረግ ነው ። እናም ይህን መሰሉ ምዝገባ ከፓርላማ አባላት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኩባንያዎች የህግ ጠበቆችና ሚኒስትሮችን እንዲሁም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን  ማካተት እንደሚገባው ነው ሁምቦርግ የሚያሳስቡት ። ጀርመን ውስጥ እጎአ ከ1972 አንስቶ   ይህን መሰሉ ምዝገባ የሚካሄደው በፈቃደኝነት ብቻ ነው ። ትርንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ድጋፍ ለማሰባሰባሰብ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚካፈሉ በ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቡድኖች አሉ ። የነዚህ ቡድኖች እንቅስቃሴ ይበልጥ ግልፅ እንዲሆንና ህዝቡም አዳዲስ ህጎች እንዴትና በነማን እንደሚቀረፁ እንዲያውቅ ፍላጎቱ መሆኑን አስታውቋል  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ