መፍትሄ ያላገኘዉ የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉዝግብ
እሑድ፣ ኅዳር 12 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዘገባዉን ሃሰት ስትል ኤርትራ በበኩልዋ ለዉድድሩ ወደ ኢትዮጵያ እንደማትሄድ አስታዉቃለች። በመሠረቱ ስፖርት በሕዝቦች መካከል ያሉ የቀለም፤ የፖለቲካ፤ የጾታ፤ የእድሜ ወዘተ ልዩነቶችና አመለካከቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ስፖርት ለወዳጅነት የሚባለዉም ለዚህ ነዉ። የሁለቱ ሀገራት እሰጣ አገባ በስፖርት እንቅስቃሴዉ ላይ ብሎም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለዉን ልዩነት እያሰፋዉ መሆኑ እሙን ነዉ። መፍትሄ ያጣዉን የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉዝግብ በተመመለከተ በአዘጋጀነዉ ዉይይት ላይ፤ ከኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ ተንታኝ ተባባሪ ፕሮፊሰር መድሕኔ ታደሰ፤ በብሪታንያ በሚኖሩ ኤርትራዉያን ማኅበረሰብ ዘንድ በስፖርት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽኦ በማድረጋቸዉ የሚታወቁት አቶ አሉላ አብርሃ፤ እንዲሁም ከሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን የወዳጅነት መድረክ ተጣማሪ ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ አንለይ ተካፍለዋል።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ