1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መጤና ተዛማች ዝርያዎች (IAS)

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001

መጤና ተዛማች ዝርያዎች አንዳንዴም መጤና ተዛማች አረሞች ሲባሊ እንሰማለን። አረም ሲል ተክሎችን ብቻ ይመለከታል። ተክሎቹ እንግዳ በሆኑበት አካባቢ የሚያስከትሉት ችግር ነዉ ይህን ስም ያሰጣቸዉ።

https://p.dw.com/p/I6Pi
ይህን በረሃ ለማለምለም የታሰበዉ መጤ ተክልምስል DW-TV

ግን እንሰሳትም መጤ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በእኛዉ አገር በዝዋይ ሐይቅ ከመጀመሪ ይገኝ የነበረዉ የዓሣ ዓይነትና ዛሬ በብዛት ያለዉ አንድ አይደለም። ነባሩን አዲሱ ዝርያ እየበላዉ ቁጥሩን እንዳመናመነዉ እዚያዉ የሚገኙና ከሐይቁ ጋ ብዙ ዘመን የኖሩ ዓሣ አጥማጆች ይናገራሉ። እዚህ ጀርመን አገርም የዉሻና ድመቶችን ዝርያ ሳይቀር ከሌላ አገር አምጥተዉ በማላመድ አራብተዉና አሳድገዉ ሲያበቁ ዛሬ እነዚያ መጤዎቹ ነባሮቹን ዝርያዎች እየጎዱ መሆኑ ማነጋገር ጀምሯል።

ሸዋዬ ለገሠ