መገናኛ ብዙሃን በሶማሊያ24 የካቲት 2000ሰኞ፣ የካቲት 24 2000ጠንከር ባለ መልኩ የታጠቁ የሶማሊያ መንግስት ኃይሎች በመቃዲሾ የሚገኙ ሶስት የግል ራዲዮ ጣቢያዎችን በትናንትዉ ዕለት በመዉረር ስርጭታቸዉን እንዲያቆሙ አስገድደዋል።https://p.dw.com/p/E0Xpጫና የበዛበት ድምፅ..........ማስታወቂያራዲዮ ሲምባ፤ ሆርን አፍሪክና ራዲዮ ሸበሌ በተሰኙት ሶስቱ የሶማሊያ የአገር ዉስጥ ራዲዮዎች የገቡት መሳሪያ አንጋቢ ኃይሎች አንዳንድ ንብረቶችን በመሰባበር፤ ሙያዊ መሳሪያዎችን ከቀሙ በኋላ ያለምንም ማብራሪያ ስፍራዉን ለቀዉ ሄደዋል።