መኢአድ ና የምርጫ ቦርድ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 19 2004ማስታወቂያ
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኅልውናዬ ላይ አደጋ ጋርጦበታል ሲል አስታወቀ። ምርጫ ቦርድ፤ በበኩሉ ፤ መ ኢ አ ድ ስም አጥፍቷልና በህግ ሊያስጠይቀው ይችላል ማለቱንም ታደሰ እንግዳው የላከልን ዘገባ ያስረዳል። መ ኢ አ ድ ፤ ትናንት ባወጣቸው 3 የተለያዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎችና በጽ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ፣ በአዲስ መልክ ህዝብ የማፈናቀል ፤ የማሠርና የማሳዳድ ዘመቻ በአፋር ክልልም ተጀምሯል ሲል አስታውቋል።
ታደሰ እንግዳው
ተክሌ የኋላ